የስነምግባር ክፍል

መልስ - ነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "ከአማኞች መካከል እጅግ የተሟላ ኢማን ያላቸው እነዚያ ይበልጥ መልካም ስነ-ምግባርን የተላበሱት ናቸው።" ቲርሚዚይ እና አሕመድ ዘግበውታል።

መልስ-1- ምክንያቱም የላቀው አላህ እንዲወደን ምክንያት ስለሆነ፤
2- ፍጡራንም እንዲወዱን ምክንያት ስለሆነ፤
3- የውመል ቂያማ ሚዛን ላይ ከባድ ምንዳ ያለው ስለሆነ፤
4- ሽልማትና ምንዳ በመልካም ስነምግባር ምክንያት ስለሚበዛ፤
5- ኢማን የተሟላ ለመሆኑም ምልክት ስለሆነ ነው።

መልስ- ከተከበረው ቁርኣን ነው። የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦ {ይህ ቁርኣን ወደዚያች እርሷ ቀጥተኛ ወደ ሆነችው መንገድ ይመራል።} [ሱረቱል ኢስራእ፡ 9] እንዲሁም ከነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሱና የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋልና፡- "እኔ የተላክሁት የተስተካከለ ስነምግባርን ላሟላ ነው።" አሕመድ ዘግበውታል።

መልስ- ኢሕሳን፡- ሁል ጊዜም ቢሆን አላህ ይመለከተኛል ማለትና ለፍጥረታትም በጎ ማድረግ እና መልካም መሆን ነው።
ነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ “የላቀው አላህ ሁሉም ነገር በመልካም መንገድ እንዲከናወን ወስኗል።" ሙስሊም ዘግበውታል።
ከኢሕሳን መገለጫዎች መካከል:

* አላህን ሲያመልኩ ሊኖር የሚገባው ኢሕሳን: ይሀውም በአምልኮ ኢኽላስ መኖር ለርሱ ጥርት ማድረግ ነው።
* ለወላጆች በንግግርም በተግባርም ደግ መሆን ነው።
* ለዘመዶች እና ለቅርብ ቤተሰቦች የሚኖር ኢሕሳን (በጎነት)
* ለጎረቤት የሚደረግ በጎነት
* ወላጅ አባታቸውን ላጡ ህፃናትና ለሚስኪኖች የሚደረግ በጎነት
* ክፉ ለሠራብን ሰው የሚደረግ በጎነት
* በንግግር ወቅት የሚደረግ በጎነት
* በውይይት ወቅት የሚደረግ በጎነት
* ለእንስሳት የሚደረግ በጎነት

መ -የበጎነት ተቃራኒ ክፋት ነው።
* ከነዚህም መካከል፡- አላህን ሲያመልኩ ኢኽላስ በሌለው መልኩ ማምለክ፤
* ወላጆችን ማመፅ፤
* ዝምድናን መቁረጥ
* መጥፎ ጉርብትና
* ለድሆች እና ለሚስኪኖች ሊኖር ከሚገባው ኢሕሳን (መልካምነት) ማፈግፈግ እና ሌሎችም የክፋት መገለጫዎች ላይ መገኘት ነው።

መልስ-
1- የላቀው አላህ መብቶችን የመጠበቅ አደራ፤
መገለጫዎቹ፡- እንደ ሶላት፣ ዘካ፣ ጾም፣ ሐጅ እና ሌሎችንም አላህ በኛው ላይ ግዴታ ያደረጋቸውን ዒባዳዎች የመተግበር አማና፤
2 - የፍጥረታትን ሐቆች የመጠበቅ አማና:
· የሰዎችን ክብር
· ገንዘባቸውንም
· ህይወታቸውንም በመጠበቅ
· እንዲሁም ምስጢራቸውንና ሰዎች በአደራ መልኩ የሰጡት ሁሉ በዚሁ የሚጠቃለል ነው።
የላቀው አላህ ስለሚድኑት ሰዎች ባህርያት ሲገልፅ እንዲህ ብሏል:- {እነዚያም እነርሱ ለአደራዎቻቸውና ለቃል ኪዳናቸው ጠባቂዎች። 8} [ሱረቱል ሙሚኑን፡ 8]

መልስ - ተቃራኒው ከዳተኝነት ሲሆን ይህም ማለት የልዕለ ኋያሉ አላህንም የሰዎችንም ሐቅ መጣስ ነው።
ነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "የሙናፊቅ ምልክቱ ሦስት ነው..." - ከነዚህም አንዱ - "አደራ ሲሰጠው ይከዳል።" ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

መልስ - ከእውነታው ጋር የሚገጥመውን ወይም ነገሩን ባለበት ተጨባጭ መናገር ነው።
ከመገለጫዎቹ መካከል፡-
ከሰዎች ጋር በመነጋገር ላይ የሚኖር ሐቀኝነት:

ቃል ኪዳንን ማክበር፤
በእያንዳንዱ ቃልም ይሁን ድርጊት ላይ ሓቀኛ ሆኖ መገኘት፤
ነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "እውነት ወደ ጽድቅ ይመራል፤ ጽድቅም ወደ ጀነት ይመራል፤ ሰውም ሓቀኛነት ማንነቱ እስኪሆን ድረስ እውነትን በመናገር ላይ ይቀጥላል።" ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

መልስ - ተቃራኒው ውሸት ነው። ይሀውም ከእውነት ጋር ተቃርኖ መገኘት ሲሆን ሰዎችን መዋሸት፣ ቃል ኪዳኖችን ማፍረስ እና የሀሰት ምስክርነትን የመሰሉ ባህርያት ማለት ነው።
ነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ ውሸት ወደ አመፀኝነት ይመራል፤ አመፀኝነት ደግሞ ወደ (ጀሀነም) እሳት ይመራል፤ ሰውም ውሸታም ተብሎ አላህ ዘንድ እስኪመዘገብ ድረስ ውሸትን በመናገር ላይ ይቀጥላል።" ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ነብዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "የሙናፊቅ ምልክቱ ሦስት ነው..." - ከነዚህም አንዱ - "ሲናገርም ይዋሻል ቃል ሲገባም ቃሉን ያፈርሳል።" ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

መልስ- - የላቀው አላህን በመታዘዝ ላይ የሚደረግ ትዕግስት፤
- አላህን ከማመፅ በመታቀብ ላይ የሚደረግ ትዕግስት፤
- በአሳማሚ የአላህ ውሳኔ ላይ የሚደረግ የሚደረግ ትዕግስት እና በማንኛውም ሁኔታ ሆኖ አላህን ማመስገን ነው።
የላቀዉ አላህ እንዲህ ብሏል፦ {አላህም ትዕግስተኞችን ይወዳል። 146} [ሱረቱ ኣሊ-ዒምራን፡ 146] ነብዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "የሙእሚን ጉዳዩ ምንኛ ድንቅ ነው?! ጉዳዩ ሁሉ ለርሱ መልካም ነው። ይህ ደግሞ የሚሆነው ለሙእሚን ብቻ ነው። መልካምን ባገኘ ጊዜ አላህን ያመሰግናል ያ ነገር ለርሱ መልካም ይሆንለታል። ችግርም ባጋጠመው ጊዜ ይታገሳል ያ ነገር ለርሱ መልካም ይሆንለታል። ሙስሊም ዘግበውታል።

መልስ - - ተቃራኒው አላህን በመታዘዝ ላይ ትዕግስት ማጣት፤ አላህን ከማመፅ በመታቀብ ላይ ትዕግስት ማጣት እና አስቀድሞ በተወሰነ እጣፈንታ በቃልም ይሁን በተግባር መበሳጨት ነው።
ከመገለጫዎቹ መካከል፦
§ ሞትን መመኘት
§ ፊትን መምታት፤
§ ልብስን መቅደድ፤
§ ፀጉርን መንጨን፤
§ ራስን መርገም፤
ነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ “የምንዳ መጠኑ በመከራው ልክ ነው። የላቀው አላህ ሰዎችን በወደደ ጊዜ ይፈትናቸዋል፤ ወደው ለተቀበሉት የአላህን ውዴታ ሲያተርፉ የተበሳጩት ደግሞ የአላህን ብስጭት ያተርፋሉ።" ቲርሚዚይ እና ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል።

መልስ - ይህ ማለት ትክክለኛ እና መልካም በሆነ ነገር ሰዎች በመካከላቸው መተጋገዛቸው ነው።
የትብብር (መረዳዳት) መገለጫዎች፦
o መብቶችን ወደ ባለቤታቸው ለመመለስ መተባበር፤
o ጨቋኝን በማቀብ ላይ መተባበር፤
o የሰዎችንም የችግረኞችንም ጉዳይ በማሳካት ላይ መተባበር፤
o በበጎ ነገር ሁሉ መተባበር፤
o በሃጢያት፣ በጥቃት እና በጠላትነት ላይ አለመተባበር ናቸው።
የላቀዉ አላህ እንዲህ ብሏል፦ {በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ። ግን በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ። አላህንም ፍሩ። አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና። 2} [ሱረቱል ማኢዳህ፡ 2] ነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "ማንኛውም ሙእሚን ከሌላ አማኝ ጋር ያለው ግንኙነት እንደ ህንጻ (ጡቦች) ነው፤ አንዱ ሌላኛውን ያጠናክራል።" ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ነብዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "ሙስሊም ለሙስሊም ወንድሙ ነው። በመሆኑም አያታልለው፣ አይዋሸው፣ ለጠላት አሳልፎ አይስጠው። የሙስሊምን ጉዳይ ለፈፀመ አላህ ጉዳዩን ይፈፅምለታል፤ የወንድሙን ችግር ላስወገደ አላህ በትንሣኤ ቀን ከችግሮቹ አንዱን ያነሳለታል። የሙስሊምን ነውር ለሸፈነ አላህ በትንሣኤ ቀን ነውሩን ይሸፍንለታል።" ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

መልስ-1- ከአላህ ሐያእ ማድረግ ማለት፡- ጥራት ይገባውና እርሱን ባለማመፅ የሚገለፅ ነው።
2- ከሰዎች ሐያእ ማድረግ ማለት፡- ይህም ጸያፍና ስድ ቃላቶችን በማስወገድ እና ሀፍረተ ገላንም ባለመገላለጥ የሚገለፅ ነው።
የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "ኢማን ከሰባ በላይ ቅርንጫፎች አሉት - ወይም ከስልሳ በላይ ቅርንጫፎች አሉት - ከፍተኛው 'ላ ኢላሀ ኢለላህ' የሚለው ቃል ሲሆን ትንሹ ደግሞ አስቸጋሪ ነገርን ከመንገድ ማስወገድ ነው። ሐያእም የኢማን ቅርንጫፍ ነው።" ሙስሊም ዘግበውታል።

መልስ- - ለአረጋውያን መራራት እና እነርሱንም ማክበር፤
- ለወጣቶች እና ለልጆች መራራት፤
- ለድሆች፣ ለሚስኪኖች እና ለችግረኞች መራራት፤
- በማብላትና ባለማስቸገርም ለእንስሳት መራራት፤
- ከነዚህም መካከል ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ያሉት ይገኝበታል፡- "አማኞች በመካከላቸው ያለው ደግነታቸው፣ ርህራሄያቸው እና መተዛዘናቸው ልክ እንደ አንድ አካል ናቸው። አንዱ አካል ሲሰቃይ መላ ሰውነት የህመም እና የትኩሳት ምላሽ ይሰጣል።" ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "አዛኞች እጅግ በጣም አዛኝ የሆነው አላህ ያዝንላቸውል፤ በምድር ላሉት እዘኑ በሰማይ ያለው (አላህ) ያዝንላችኋል።" አቡዳውድና ቲርሚዚይ ዘግበውታል።

መልስ - የላቀው አላህን መውደድ።
የላቀዉ አላህ እንዲህ ብሏል፦ {እነዚያ ያመኑትም አላህን በመውደድ (ከነርሱ) ይበልጥ የበረቱ ናቸው።} [ሱረቱል በቀራህ 165]
የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንን መውደድ።
እንዲህ ብለዋል፦ "ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! ማናችሁም ዘንድ ከአባቱ፣ ከልጁና ከሰው ልጆች ሁሉ ለርሱ ይበልጥ ተወዳጁ እኔ እስካልሆንኩለት ድረስ እምነታችሁ አልተሟላም።" ቡኻሪይ ዘግበውታል።
ምእመናንን መውደድ፤ ለራስህ የምትወደው መልካም ነገርንም ለነርሱም ልትወድላቸው ይገባል።
ነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "ማናችሁም ለራሱ የሚወደውን ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ እምነቱ አልተሟላም።" ቡኻሪይ ዘግበውታል።

መልስ - ሰዎችን ሲያገኙ በፍካት ደስታንና አዛኝነትን ፊት ላይ አጉልቶ ማንፀባረቅ ነው።
ሰዎችን የሚያርቃቸው ከሆነው ፊትን የማኮሳተር ተቃራኒ ነው።
የፈገግታን የላቀ ደረጃ በተመለከተ ብዙ ሐዲሦች የመጡ ሲሆን ከነዚህም መካከል ከአቡ ዘር (ረዲየላሁ ዐንሁ) በተላለፈ ሐዲሥ ነብዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ እንዳሏቸው ገልፀዋል፡- "ወንድምህን በፈገግታ የተሞላ ፊት ማሳየትንም ቢሆን መልካም ነገርን እንደ ቀላል ነገር አድርገህ አትመልከት።" ሙስሊም ዘግበውታል። የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "በወንድምህ ፊት ፈገግ ማለትህም ምጽዋት ነው።" ቲርሚዚይ ዘግበውታል።

መልስ- ምቀኝነት ማለት ፀጋ ከሌሎች እንዲወገድ መመኘት ወይም ሌሎች ፀጋ ማግኘታቸውን መጥላት ነው።
የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦ {«ከምቀኛም ክፋት በተመቀኘ ጊዜ፤ (እጠበቃለሁ በል)።»} [ሱረቱል ፈለቅ፡ 5]
አነስ ቢን ማሊክ አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸው እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "እርስ በርሳችሁ አትጠላሉ፣ አትመቀኛኙ፣ ጀርባም አትሰጣጡ፤ የአላህ ባርያ ወንድማማቾች ሁኑ።" ቡኻሪይ እና ሙስሊም ዘግበውታል።

መልስ - መሳለቅ ሙስሊም ወንድምህ ላይ ማፌዝና ማሳነስ ነው። ይህ ደግሞ አይፈቀድም።
የላቀው አላህ ከዚህ ሲከለክለን እንዲህ ብሏል፦ {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ወንዶች ከወንዶች አይቀልዱ። ከእነርሱ የበለጡ ሊኾኑ ይከጀላልና። ሴቶችም ከሴቶች (አይሳለቁ)። ከእነርሱ የበለጡ ሊሆኑ ይከጀላልና። ነፍሶቻችሁንም አታነውሩ። በመጥፎ ስሞችም አትጠራሩ። ከእምነት በኋላ የማመጽ ስም ከፋ። ያልተጸጸተም ሰው እነዚያ እነርሱ በዳዮቹ ናቸው።11} [ሱረቱል ሁጁራት፡ 11]

መልስ - ትሕትና ማለት የሰው ልጅ ራሱን ከሌሎች የተሻለ አድርጎ ላያይ፤ ሰውንም ላይንቅና እውነታንም ላይገፈትር (ሊቀበል) ነው።
የላቀዉ አላህ እንዲህ ብሏል፦ {የአርረሕማንም ባሮች እነዚያ በምድር ላይ በዝግታ የሚሄዱት... ናቸው።} [ሱረቱል ፉርቃን፡ 63] ማለትም፡ ትሁት ሆነው። የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "ማናችሁም ራሱን ለአላህ ብሎ ዝቅ ካደረገ አላህ ከፍ ያደርገዋል።" ሙስሊም ዘግበውታል። በሌላም ሐዲሥ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህም ብለዋል፦ “ማንም ሰው ሌላው ላይ ድንበር እስከማይተላለፍና አንዱ በሌላው ላይም እስከማይመፃደቅ ድረስ እርስ በርሳችሁ ትሑት ትሆኑ ዘንድ አላህ ወደኔ ወሕይ (መለኮታዊ ራእይ) አውርዶልኛል።" ሙስሊም ዘግበውታል።

መልስ-1- በእውነት ላይ መኩራራት፡ እውነትን መገፍተርና አለመቀበል ነው።
2- በሰዎች ላይ መኩራራት፡ ሰዎችን ማቃለልና ማንቋሸሽ ነው።
የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "በልቡ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያክል ኩራት ያለበት ጀነት አይገባም።" አስከትሎ አንድ ሰው፡- "የሆነ ሰው ልብሱም ጥሩ፣ ጫማውም ጥሩ እንዲሆን ቢወድስ? ሲል እርሳቸውም፦ "አላህ ውብ ነው፤ ውብ ነገርንም ይወዳል። ኩራት ማለት እውነታን መገፍተርና ሰዎችን መናቅ ነው።" ሙስሊም ዘግበውታል።
- እውነታን መገፍተር ማለት እውነትን አለመቀበል ማለት ነው።
- ሰዎችን መናቅ ሲባል ደግሞ ሰዎችን አሳንሶ ማየት ነው።
- ጥሩ ቀሚስ እና ጥሩ ጫማ መልበሱ ኩራት አይደለም።

መልስ - በመግዛትና በመሸጥ ላይ ማጭበርበር፡ ይህም የሸቀጦችን እንከን በመደበቅ ሊሆን ይችላል፤
- በመማር ማስተማር ማጭበርበር፡ ተማሪዎች በፈተና ጊዜ መኮረጃቸውን ይመስል፤
- በቃል ማጭበርበር፡ የውሸት ምስክርነትንና ውሸትን ይመስል፤
- ከሰዎች ጋር የተስማሙትን ቃል አለመሙላትን መጥቀስ ይቻላል።
የማጭበርበር ክልከልነትን በተመለከተ የአላህ መልእክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በአንድ የእህል ክምር በኩል እያለፉ ሳሉ እጃቸውን ወደ እህሉ አስገቡና ጣቶቻቸው አንዳች እርጥበት ሲያገኘው እንዲህ አሉ፡- “የእህሉ ባለቤት ሆይ! ይህ ምንድን ነው?” እርሱም፡- "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ዝናብ መትቶት እኮ ነው" አላቸው። እሳቸውም እንዲህ አሉት፦ "(የእርጥብ ክፍሉን) ሰዎች እንዲያዩት ከክምሩ በላይ በኩል ለምን አላስቀመጥከውም? የሚያጭበረብር ከኛ አይደለም።" ሙስሊም ዘግበውታል።
በሐዲሡ "አስ-ሱብራ" የተባለው የእህል ክምሩ ነው።

መልስ - ሙስሊም ወንድምህ በሌለበት ጊዜ በሚጠላው በኩል ማውሳት ነው።
የላቀዉ አላህ እንዲህ ብሏል፦ {ከፊላችሁም ከፊሉን አይማ። አንደኛችሁ የወንድሙን ስጋ የሞተ ኾኖ ሊበላው ይወዳልን? (መብላቱን) ጠላችሁትም፤ (ሐሜቱንም ጥሉት)። አላህንም ፍሩ። አላህ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና። 12} [ሱረቱል ሑጁራት፡ 12]

መልስ - ሀሜት ማለት በሰዎች መካከል ችግር ለመፍጠር ወሬ ማመላለስ ነው።
የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "ውሸት አመላላሽ ጀነት አይገባም።" ሙስሊም ዘግበውታል።

መልስ- መልካም ነገርን ወይም ደግሞ ማድረግ የሚጠበቅበትን ነገር ከማድረግ መስነፍ ነው።
ግዴታ ነገራቶችን ከማድረግ መሰላቸትን እንደምሳሌ መጥቀስ ይቻላል።
የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦ {መናፍቃን አላህን ያታልላሉ። እርሱም አታላያቸው ነው። (ይቀጣቸዋል)። ወደ ሶላትም በቆሙ ጊዜ ታካቾች ስዎችን የሚያሳዩ ሆነው ይቆማሉ። አላህንም ጥቂትን እንጅ አያወሱም። 142} [ሱረቱ-ኒሳእ፡ 142]
በመሆኑም ሙእሚን ስልቹነትን፣ መኮፈስንና ስንፍናን ትቶ በዱኒያዊ ጉዳዩም ቢሆን አላህን በሚያስደስት ሥራና እንቅስቃሴ በትጋትና በጥረት ሊጣደፍ ይገባዋል።

መልስ-1- የተመሰገነ ቁጣ፡- ይሀውም ከሓዲዎች፣ ሙናፊቆችም ሆኑ ሌሎች የአላህን ድንበር ሲጥሱ ለአላህ ተብሎ የሚደረግ ቁጣ ነው።
2- የተወገዘ ቁጣ፡- ይኸውም አንድ ሰው ማድረግ የማይገባውን እንዲያደርግና እንዲናገር የሚያደርገው የቁጣ ዓይነት ነው።
ለተወገዘው የቁጣ ዓይነት መፍትሄው፦
ውዱእ ማድረግ፤
ቆሞ ከነበረ መቀመጥ፤ ተቀምጦ ከነበረ ደግሞ መጋደም፤
በዚህ ረገድ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ያስተላለፉትን ትእዛዝ መተግበር፡- “አትቆጣ!"
በተናደደ ጊዜ በስሜታዊነት ሌላ ነገር ውስጥ እንዳይገባ ራስን መቆጣጠር፤
"አዑዙ ቢላህ" ብሎ ከተረገመው ሰይጣን ተንኮል በአላህ መጠበቅ፤
ዝምታ።

መልስ - የሰዎችን ነውርና የሚደብቁትንም ነገር መፈላፈልና ማጋለጥ ነው።
ከተከለከሉት መገለጫዎቹ መካከልም፡-
በቤት ውስጥ የሰዎችን የግል ክፍሎች ማየት፤
ሰዎቹ ሳያውቁ ወሬያቸውን ማዳመጥ፤
የላቀዉ አላህ እንዲህ ብሏል፦ {ነውርንም አትከታተሉ ...} [ሱረቱል ሑጁራት፡ 12]

መልስ - አባካኝነት ማለት፡ ገንዘብን ተገቢ ባልሆነ መልኩ ማውጣት ነው።
ተቃራኒው ደግሞ ስስት ሲሆን፡ ገንዘብ ሊወጣበት ለሚገባው ነገር ከማውጣት መታቀብ ነው።
ትክክለኛው ነገር በመካከላቸው ያለው (ለጋስነት) ነው። ሙስሊም ለጋስ ነው መሆን ያለበት።
የላቀዉ አላህ እንዲህ ብሏል፦ {እነዚያም በለገሱ ጊዜ የማያባክኑ የማይሰስቱትም ናቸው። በዚህም መካከል (ልግስናቸው) ተክክለኛ የሆኑ ናቸው። 67} [ሱረቱል ፉርቃን፡ 67]

መልስ- ፈሪ መሆን ማለት፡- መፈራት የሌለበትን ነገር መፍራት ነው።
ሐቅን ከመናገር እና ክፋትን ከመከልከል መፍራት ነው።
ጀግንነት ማለት ደግሞ፡- ከእስልምና እና ከሙስሊሞች ለመከላከል በጂሃድ የጦር አውድማዎች ግንባር ቀደም መሆንን የመሳሰሉ እውነታዎች ላይ ፊት ለፊት መሆን ነው።
ነብዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በዱዓያቸው እንዲህ ብለዋል፡- "አላህ ሆይ! ፈሪ ከመሆን ባንተ እጠበቃለሁ።" የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "ጠንካራው አማኝ ከደካማው አማኝ ይልቅ አላህ ዘንድ የተሻለ እና የተወደደ ነው።ምንም እንኳን ሁሉም ዘንድ መልካም ነገር አለ።" ሙስሊም ዘግበውታል።

መልስ - ለምሳሌ እርግማን እና ስድብ፤
እገሌ "እንስሳ" ነው ማለት ወይም መሰል የቃል አጠቃቀምን ይመስል፤
ወይም የብልግናና አፀያፊ ነውሮችን መናገር፤
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ይህን ሁሉ ከልክለዋል፤ እንዲህም ብለዋል፦ “ሙእሚን ዘላፊ፤ ተራጋሚም፤ ወይም ባለጌ አልያም ስድ አይደለም።" ቲርሚዚይ እና ኢብኑ ሒባን ዘግበውታል።

መልስ-1- መልካም ስነምግባር እንዲቸርህና በዛ ላይም እገዛውን እንዲለግስህ ዱዓእ ማድረግ፤
2- ልዕለ ኋያሉ አላህ እንደሚቆጣጠርህ፣ እንደሚሰማህ እና እንደሚያይህ አስበህ ማስተዋል፤
3- የመልካም ስነምግባርን ምንዳ እና ጀነት ለመግባት ምክንያት መሆኑን ማስታወስ፤
4- የመጥፎ ስነ ምግባርን መዘዝ እና ወደ እሳትም ለመግባት ምክንያት መሆኑን ማስታወስ፤
5- መልካም ሥነ ምግባር የአላህንም የፍጡራንንም ውዴታ እንደሚያተርፍልህ፤ በተቃራኒው መጥፎ ሥነ ምግባር ደግሞ የአላህም የፍጡራንም እንደሚያስከትልብህ ማወቅ።
6- የነቢዩን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የህይወት ታሪክ ማንበብ እና ፋናቸውን መከተል፤
7- ከጥሩ ሰዎች ጋር መቀራረብ እና ከመጥፎ ሰዎች ደግሞ መራቅ ነው።