የፊቅህ ክፍል

መልስ- ጠሃራ (ንጽህና) ማለት፡- ሐደሥን እና ቆሻሻን ማስወገድ ነው።
ጠሃረቱል ኸበሥ (ቆሻሻን የማስወገድ ንጽህና)፡- ይህም ማለት ሙስሊሙ በሰውነቱ፣ በልብሱ፣ ወይም በሚሰግድበት ቦታና ዙርያ ያረፈ ነጃሳ ነገርን ማስወገዱ ነው።
ጠሀረቱል ሐደሥ (ከርኩሰት ለመጽዳት የሚደረግ ንጽህና)፡- ይህም ማለት ውዱእ ማድረግን ወይም ገላ መታጠብን የሚያስገድድ ነው፤ ውሃ በታጣ ወይም መጠቀም ባልተቻለ ጊዜ ደግሞ ተየሙም ማድረግን የሚጠይቅ የንጽህና ዓይነት ነው።

መልስ- ንፁህ እስኪሆን ድረስ በውሃ በማጠብ ይፀዳል።
- ይሁን እንጅ ነጃሳው የውሻ ለሀጭ ከሆነ የመጀመሪያውን በአፈር አድርጎ ሰባት ጊዜ መታጠብ ይጠበቅበታል።

መልስ - ነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "አንድ ሙስሊም ባሪያ" - ወይም "አማኝ የሆነ ሰው" - "ውዱእ በሚያደርግበት ጊዜ ፊቱን ሲያጥብ በዓይኑ የተመለከተው ኃጢአት ሁሉ ከፊቱ ከውኋው ጋር አብሮ ይፀዳለታል።” - ወይም “ከመጨረሻው የውሃ ጠብታ ጋር አብሮ ይራገፍለታል።” - “እጁን ሲታጠብም እንዲሁ እጆቹ እየዳሰሰች የፈፀመችው ኋጢአት ከውኋው ጋር አብሮ ይፀዳለታል።" - ወይም “ከመጨረሻው የውሃ ጠብታ ጋር አብሮ ይራገፍለታል።” - “እግሩን ሲታጠብም እንዲሁ እግሮቹ ስትራመድ የፈፀመችው ኋጢአት ከውኋው ጋር አብሮ ይፀዳለታል።" - ወይም “ከመጨረሻው የውሃ ጠብታ ጋር አብሮ ይራገፍለታል።” - “ልክ እንደዚሁ እያለ ከኃጢአት ንጹሕ እስኪሆነ ድረስ ይፀዳል።" ሙስሊም ዘግበውታል።

መልስ - እጆችን ሶስት ጊዜ ማጠብ።
ሶስት ጊዜ መግመጥሞጥ እና ውኋ ወደ አፍንጫ ውስጥ ሳብ አድርጎ አፍንጫን አጥርቶ ውኋውን ወደ ውጭ መመለስ።
አፍን መግመጥሞጥ፡- ውሃን በአፍ ውስጥ አስገብቶ ውኋውን ማማታትና ከዚያም መትፋት ነው።
"ኢስቲንሻቅ" ሲባል:
ውሃውን በቀኝ እጅ ይዞ በአየር ወደ አፍንጫው ውስጥ መሳብ ነው።
"ኢስቲንሣር" ሲባል ደግሞ: "ኢስቲንሻቅ" ሲያደርጉ ወደ አፍንጫ የሳቡትን ውኋ በግራ እጅ ወደ ውጭ ማስወጣት ነው።
ከዚያም ፊትን ሦስት ጊዜ ማጠብ
ከዚያም እጆችን እስከ ክርኖች ድረስ ሶስት ጊዜ ማጠብ
ከዚያም ጭንቅላትን ማበስ፤ በሁለቱ እጆች ከግንባር ተነስቶ ወደ ማጅራት አብሶ ወደ ግንባር በመመለስ ካበሱ በኋላ ጆሮዎችን ማበስ ነው።
ከዚያም እግርን እስከ ቁርጭምጭሚት ድረስ ሶስት ጊዜ ማጠብ
ይህ የተሟላ የሆነው የውዱእ አደራረግ ሲሆን ይህም ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ዑሥማን፣ ዐብዱላህ ቢን ዘይድ እና ሌሎችም ያስተላለፉ እንዲሁም በቡኻሪይ እና ሙስሊም የተዘገበ ሐዲሥ ላይ የተገለጸ ነው። እንዲሁም በቡኻሪይ እና በሌሎችም ዘገባዎች እንዲህ መባሉ ተረጋግጧል፡- “አንድ አንድ ጊዜም ውዱእ አድርገዋል፤ ሁለት ሁለት ጊዜም ውዱእ አድርገዋል።” ማለትም፡ እያንዳንዱን የውዱእ ክፍል አንድ አንድ ጊዜም ሁለት ሁለት ጊዜም እያጠቡ ውዱእ ያደርጉ ነበር ነው።

መልስ - እነዚህ የትኛውም ሙስሊም ውዱእ ሲያደርግ አንዱንም ቢተው ያደረገው ውዱእ ትክክል የማይሆነለት ነው።
1- ፊትን መታጠብ መጉመጥመጥ እና አፍንጫን ጨምሮ ማጠብ ፤
2- እጅን እስከ ክርኖች ማጠብ፤
3- ጆሮን ጨምሮ ጭንቅላትን ማበስ፤
4- እግርን እስከ ቁርጭምጭሚት ድረስ ማጠብ፤
5- በውዱእ አካላት መካከል ያለውን ቅደም ተከተል መጠበቅ: ማለትም ፊትን ማጠብ፤ ከዚያም እጆችን ማጠብ፤ ከዚያም ጭንቅላትን ማበስና ከዚያም እግሮችን ማጠብ ነው።
6- ማከታተል፡- ማለትም ውዱእ ሲያደርጉ ከአንደኛው የውዱእ አካል ወደ ሌላኛው ሲሸጋገሩ አካላቱ እስኪደርቅ ድረስ ሳይዘገዩ ማከታተል ነው።
- ማለትም ግማሹን የዉዱእ አካላት አዳርሰው ዘግይቶ ከቆይታ በኋላ ወደሌላኛው አካል መሸጋገሩ ዉዱኡ ትክክለኛ እንዳይሆን ያደርገዋል።

መልስ - የዉዱእ ሱናዎች የሚባሉት፡- ከሰሩት ተጨማሪ አጅር እና ምንዳን የሚያስገኝ ሲሆን ካልሰሩት ግን ወንጀል አይደለም ዉዱኡም ትክክል ነው።
1 - "ቢስሚላህ" ብሎ በአላህን ስም መጀመር
2- ሲዋክ መጠቀም (ጥርስን መፋቅ)
3 - የእጅ መዳፎችን ማጠብ
4- ጣቶችን ፈልፍሎ ማጠብ
5- የአካል ክፍሎችን ሲያጥቡ ሁለተኛና ሦስተኛ ጊዜ መድገም
6- በቀኝ መጀመር
7- ከዉዱእ በኋላ የሚከተለውን ዚክር ማለት፡- "አሽሀዱ አን ላኢላሃ ኢለሏህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ ወአሽሀዱ አነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ" ትርጉሙም: ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚገዙት አምላክ እንደሌለና ተጋሪ የሌለው ብቸኛ መሆኑን እመስክራለሁ፤ ሙሀመድም የአላህ መልዕክተኛው እና ባሪያው መሆናቸውንም እመስከራለሁ።
8- ከኋላው ሁለት ረከዓ መስገድ

መልስ- ከፊት እና ከኋላ ካሉ ሁለቱ ቀዳዳዎች የሚወጣ እንደ ሽንት፣ ሰገራ ወይም ንፋስ ያለ ነገር ሁሉ፤
እንቅልፍ መተኛት፣ እብደት ወይም ራስን መሳት፤
የግመል ሥጋ መብላት፤
ያለግርዶሽ ብልትን ወይም ፊንጢጣን በእጅ መንካት፤

መልስ- ተየሙም ማለት፡- ውሃ ሲጠፋ ወይም መጠቀሙ በማይመችበት ጊዜ አፈር ወይም ሌላ የምድር አካልን በውኋ ምትክ መጠቀም ነው።

መልስ- አፈሩን አንድ ጊዜ በመዳፍ እጅ መታ አድርጎ የእጆችን ጀርባ እና ፊትን ማበስ ነው።

መልስ- ውዱእን የሚያፈርሱ ነገሮች ሁሉ፤
እና ውሃ ከተገኘ

መልስ- ኹፍ የሚባለው፡- እግር ላይ የሚለበስ ሆኖ ከቆዳ የተሰራ ነው።
ካልሲ፡- ከቆዳ ውጪ በሆነ ነገር የተሰራ ሆኖ እግር ላይ የሚለበስ ነው።
እግሮችን በማጠብ ፋንታ እነርሱ ላይ ማበስ የተደነገገ ነው።

መልስ - በተለይም በቀዝቃዛ በክረምት እና በጉዞ ወቅት በእግር ላይ የተጠለቀውን ነገር ማውለቁ አስቸጋሪ በሚሆንበት ጊዜ አላህ ለባርያዎቹ የደነገገላቸው ማግራራት እና ማቅለል ነው።

መልስ-1- ኹፉን የሚለብሰው ጠሃራ ሆኖ ማለትም ከውዱእ በኋላ መሆን አለበት።
2- ኹፎቹ ጠሃራ መሆን አለባቸው፤ ነጃሳ ላይ ማበስ አይፈቀድምና።
3- ኹፎቹ ውዱእ ሲደረግ መታጠብ ያለበትን ቦታ የሚሸፍኑ መሆን አለባቸው።
4- ማበሱ በተወሰነለት የጊዜ ገደብ ውስጥ መሆን አለበት፤ መንገደኛ ላልሆነ ነዋሪ፡ አንድ ቀን ከነሌሊቱ፤ መንገደኛ ደግሞ፡- ሶስት ቀናት ከነሌሊቱ ባለው ጊዜ ውስጥ ማበስ ይችላል።

መልስ- በኹፍ ላይ የማበስ አኳኋኑን በተመለከተ፡- የእጆቹን ጣቶች በውሃ በመንከር ከእግሩ ጣቶች ጀምሮ ወደ ተረከዙ ማበስ ነው። ሲያብስም የቀኝ እግሩን በቀኝ እጁ የግራ እግሩን ደግሞ በግራ እጁ ነው የሚያብሰው። በሚያብስበት ጊዜ ጣቶቹን ከፈት ያድርግ፤ መደጋገም አይጠበቅበትም።

መልስ - 1 - በኹፍ ላይ የማበስ ጊዜ ማብቂያው: መንገደኛ ላልሆነ ነዋሪ አንድ ቀን ከነሌሊቱ ለመንገደኛ ደግሞ ሶስት ቀን ከነሌሊቱ ባልነው መሰረት በሸሪዓ የተወሰነውን የማበሻ ጊዜ ካለፈ በኋላ ኹፉ ላይ የማበሻ ጊዜው ያልቃል።
2 - ኹፎቹን ማውለቅ: አንድ ሰው ኹፎቹን ወይም አንዳቸውን ካበሰባቸው በኋላ ካወለቀ በላዩ ላይ ያበሰውም አብሮ ይፈርሳል።

መልስ- ሰላት፡- በተክቢራ ተጀምሮ በሰላምታ የሚጠናቀቅ በውስጡም ልዩ የሆኑ ንግግሮችንና ተግባራትን ባካተተ መልኩ አላህን ማምለክ ነው።

መልስ- ሰላት በሁሉም ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።
የላቀዉ አላህ እንዲህ ብሏል፦ {ሰላት በምእምናን ላይ በጊዜያት የተወሰነ ግዴታ ነው። 103} [ሱረቱ-ኒሳእ፡ 103]

መልስ - ሰላትን መተው ክህደት ነው። ነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፡- "በእኛና በነሱ መካከል ያለው ቃል ኪዳን ሰላት ነው። (በመሆኑም) ሰላትን የተወ ሰው በእርግጥ ክዷል።" ኢማሙ አሕመድና ቲርሚዚይ እንዲሁም ሌሎችም ዘግበውታል።

መልስ - ሙስሊምበቀንና በሌሊት አምስት ሶላቶችን የመስገድ ግዴታ አለበት። የፈጅር ሶላት ሁለት ረከዓዎች፣ የዙህር ሶላት አራት ረከዓዎች፣ የዐስር ሶላት አራት ረከዓዎች፣ የመግሪብ ሶላት ሶስት ረከዓዎች እና የዒሻ ሶላት አራት ረከዓዎች።

መልስ - 1- ሙስሊም መሆን፤ ከካፊር ተቀባይነት የለውም።
2- አእምሮ ጤናማ መሆን: የእብድ ሰላት ትክክል አይደለም።
3- መለየት መቻል: የጨቅላ ህፃን ወይም ጥሩውን ከመጥፎ የማይለይ ሰው ሰላቱ ትክክለኛ አይደለም።
4 - ኒያ
5 - የሰላት ወቅቱ መግባት፤
6 - ከየትኛውም ዓይነት ሐደሥ ነጹህ መሆን፤
7- ከነጃሳ መፅዳት፤
8- ሀፍረተ ገላን መሸፈን፤
9- ቂብላን መቅጣጨት ናቸው።

መልስ - እንደሚከተለው አሥራ አራት ምሰሶዎች ናቸው፦
አንዱ፡- በተቻለ መጠን መቆም፤
ተክቢረቱል ኢሕራም፡ ይኸውም "አላሁ አክበር" ማለት ነው።
ፋቲሓ (አልሓምዱ)ን መቅራት፤
ጀርባን ለጥ አድርጎ በመዘርጋት እና ጭንቅላትንም በስትክክል አድርጎ ሩኩዕ ማድረግ (መጎንበስ)
ከሩኩእ መነሳት፤
ተስተካክሎ መቆም፤
ግንባርን፣ አፍንጫን፣ መዳፎችን፣ ሁለቱን ጉልበቶች እና የሁለቱን እግሮች ጣቶችን አስተካክሎ መሬት ላይ አድርጎ ሱጁድ ማድረግ፤
ከሱጁድ ቀና ማለት፤
በሁለቱ ሱጁዶች መካከል መቀመጥ፤
የአቀማመጡ ሱናው፡ ቀኝ እግርን ቀጥ አድርጎ ተክሎ የእግርን ጣቶች ደግሞ ወደ ቂብላ ካቅጣጩ በኋላ በግራ እግር የውስጠኛው ክፍል ላይ መቀመጥ።
መረጋጋት: ይሀውም በእያንዳንዱ ምሰሶም ይሁን ድርጊት ላይ መረጋጋት፤
የመጨረሻው ተሸሁድ፤
ለተሸሁዱ መቀመጥ፤
ወደሁለቱም አቅጣጫ ማሰላመት: ይሀውም ሁለት ጊዜ፡- “አሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላህ" እያሉ ነው።
ሩክኖችን - በጠቀስነው መልኩ - ማከታተል: ለምሳሌ ሆን ብሎ ሩኩዕ ሳያደርግ ሱጁድ ቢያደርግ ሶላቱ ውድቅ ይሆናል። ተዘናግቶ ከሆነ ግን ተመልሶ ሩኩዕ ካደረገ በኋላ ከዚያም ሱጁድ ያደርጋል።

መልስ - የሰላት ግዴታዎች እንደሚከተለው ስምንት ናቸው:
1- ከተክቢረተል ኢሕራም ውጭ ያሉ ተክቢራዎች፤
2- ኢማም ለሆነና ብቻውን ለሚሰግድ ሰው "ሰሚዐላሁ ሊመን ሓሚደህ" ማለቱ "ትርጉሙም፦ "አላህ የሚያመሰግኑትን ይሰማል" ነው፤
3 - "ረበና ወለከል ሓምድ" ይበል ትርጉሙም፡ “ጌታችን ሆይ! ምስጋና ላንተ ይሁን።” ነው፤
4 - «ሱብሓነ ረቢየል ዓዚም» ይበል ትርጉሙም፦ “ጥራት ይገባው ለታላቁ ጌታዬ" ነው፤
5 - «ሱብሓነ ረቢየል አዕላ» ይበል ትርጉሙም “ጥራት ይገባው ለላቀው ጌታዬ”
ነው፤
6 - «ረቢ-ግ-ፊርሊ» ይበል ትርጉሙም “ጌታዬ ሆይ!ማረኝ” ነው፤
7- የመጀመሪያው ተሸሁድ፤
8- ለመጀመሪያው ተሸሁድ መቀመጥ፤

መልስ- እንደሚከተለው አስራ አንድ ናቸው፦
1 - ከተክቢረተል ኢሕራም በኋላ እንዲህ ማለት: የመክፈቻውን ዱዓእ (ዱዓኡል ኢስቲፍታሕ) እንዲህ ማለት፡- «ሱብሓነከሏሁም ወቢሓምዲከ ወተባረከ ኢስሙከ ወተዓላ ጀዱከ ወላኢላሀ ገይሩክ» [ትርጉሙም ጥራትና ልቅና ለአንተ ይሁን አምላኬ ሆይ ምስጋናም ለአንተ ይሁን፤ ስምህም የላቀ ነው፤ ግርማህም ከፍ ከፍ ይበል፤ ካንተ በቀርም አምላክ የለም። ማለት ነው]
2 - «አዑዙ ቢላሂ ሚነ ሸይጧኒ ረጂም» ማለት፤
3 - ቢስሚላህ፤
4 - አሚን ማለት፤
5- ከአል-ፋቲሐ በኋላ ተጨማሪ ሱራን መቅራት፤
6- የኢማሙ ጮክ ብሎ መቅራት፤
7- ከምስጋናው (ሰሚዐሏሁ ሊመን ሓሚደህ ካሉ) በኋላ እንዲህ ማለት፡- ”ሚልኡ ሰማዋቲ ወሚልኡል አርዲ ወሚልኡ ማሺእተ ሚን ሸይኢን ባዕዱ“ ትርጉሙም: "ምስጋና በሰማያት ሙሉ በምድር ሙሉ ላንተ ይሁን፤ ከዚያም በኋላ በወደደህ ነገር ሙሉም ምስጋና ላንተ ይሁን።"
8- በሩኩዕ ጊዜ ከሚደረገው ተስቢሕ ወይንም ሁለተኛውና ሦስተኛው ተስቢሕ ከዚያም በላይ መጨመር
9- በሱጁድ ጊዜ ከአንድ ጊዜ በላይ የሚደረገው ተስቢሕ፤
10 - በሱጁዶች መካከል ከአንድ ጊዜ በላይ “ረቢ-ግ-ፊርሊ”
ማለት:
11 - በመጨረሻው ተሸሁድ በሳቸውም በቤተሰቦቻቸውም የአላህ ሰላት እና ሰላም እንዲሁም በረካ እንዲሰፍን ከተማፀነ በኋላ ያሻውን ዱዓእ ያድርግ።
አራተኛ፡ ድርጊታዊ የሚባሉ ሱና የሆኑ ድርጊቶች፡-
1- ተክቢረተል ኢሕራም እያደረጉ እጆችን ወደ ላይ ማንሳት፤
2 - በሩኩዕም ጊዜ (እጆችን ማንሳት)
3 - ከሩኩዕ ቀና ሲሉም (እጆችን ማንሳት)
4- ከዚያም በኋላ እጆችን አስተካክሎ ማስቀመጥ፤
5- የቀኝ እጅን በግራ እጅ ላይ ደርቦ ማስቀመጥ፤
6- ሱጁድ ወደሚያደርጉበት ቦታ መመልከት፤
7- ሲቆም በእግሮች መካከል ከፈት አድርጎ መቆም፤
8- የሁለቱ እጆች ጣቶችን ፈታ አድርጎ ጉልበትን በመያዝ፤ ጀርባን ቀጥ በማድረግ ጭንቅላትንም በጀርባ ትይዩ አድርጎ ሩኩዕ ማድረግ(መጎንበስ)
9- የሱጁድ አካላትን በመሬት ላይ አመቻችቶ እያንዳንዱ ክፍል መሬት እንዲነካ በማድረግ ሱጁድ መውረድ፤
10 - አካላትን ማራራቅ: እጆችን ከጎድን፣ ሆድን ከጭኖች፣ ጭኖችን ከተረከዞች መለየት፤ እንዲሁም ጉልበቶችን ከፈት ማድረግ፤ ተረከዞችን ቀጥ አድርጎ መትከል፤ የእግር ጣቶችን ውስጠኛው ክፍል ለያይቶ መሬት ላይ ማድረግ፤ ሁለት እጆችን ጣቶቻቸውን ገጥሞ በመዘርጋት በትከሻ ትይዩ ማድረግ፤
11- በሁለቱ ሱጁዶች መካከል እና ለመጀመሪያው ተሸሁድ ሲቀመጡ "ኢፍቲራሽ" አድርጎ መቀመጥ እና በሁለተኛው ተሸሁድ ደግሞ "ተወሩክ" በሚባለው አቀማመጥ መቀመጥ፤
12- በሁለቱ ሱጁዶች መካከል ሲቀመጡ እጆችን ጣቶቻቸውን ገጥሞ በመዘርጋት ጭን ላይ ማድረግ ነው። ምናልባት ትንሿን ጣት እና ቀለበት ጣትን ጨብጦ የመሀል ጣትን ከአውራ ጣት ጋር አብሮ ክብ እንዲሰሩ ማድረግ፤ በተሸሁድም አቀማመጡ እንዲሁ ነው።
13- አሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላህ በሚልበት ጊዜ ወደቀኝና ወደ ግራ መዞር፦

መልስ- (1) ከሰላት ቅድመ ሁኔታዎች ወይም ማዕዘናት መካከል አንዱንም ቢሆን መተው፤
(2) ሆን ብሎ መናገር፤
(2) ሆን ብሎ መብላት ወይም መጠጣት፤
(2) ተከታታይ ተደጋጋሚ እንቅስቃሴ፤
(2) ሆን ብሎ ከሰላት ግዴታዎችን አንዱን መተው፤

መልስ- የሰላት አፈጻጸም፦
1- ሳይዛነፉና ሳይዟዟሩ ሙሉ አካልን ወደ ቂብላ (ማዞር) መቅጣጨት፤
2- ከዚያም በልቡ ሊሰግደው የፈለገውን ሰላት በቃል መናገር ሳይጠበቅበት በውጡ ማሰብ፤
3 - ከዚያም "አሏሁ አክበር!" ብሎ ተክቢረተል ኢሕራም ማድረግ፤ ተክቢራውን በሚልበት ጊዜ እጅን በትከሻ ትይዩ ማንሳት፤
4- ከዚያም የቀኝ እጅን መዳፍ በግራ እጅ የመዳፍ ጀርባ ላይ አጣምሮ ደረት ላይ ማስቀመጥ፤
5- ከዚያም እንዲህ ብሎ ዱዓኡል ኢስቲፍታሕን ማለት፦ "አላሁመ ባዒድ በይኒ ወበይነ ኸጧያየ ከማ ባዐድተ በይነል-መሽሪቂ ወል-መግሪቢ አሏሁመ ነቂኒ ሚን ኸጧያየ ከማ ዩነቀ-ሥ-ሠውቡል አብየዱ ሚነ ደነስ አላሁመ 'ግሲልኒ ሚን ኸጧያየ ቢሥ-ሠልጂ ወልማኢ ወል-በረድ" ትርጉሙ፦ "አላህ ሆይ! በምሥራቅና በምዕራብ መካከል እንዳራራቅከው እኔንም ከወንጀሌ አርቀኝ፤ አላህ ሆይ! ነጭ ልብስ ከቆሻሻዎች እንደሚጸዳው እኔንም ከወንጀሌ አጥራኝ፤ አላህ ሆይ! እኔን ከወንጀሌ በውሃ እና በፈሳሹም በደረቁም በረዶ እጠበኝ።"
ወይም እንዲህ ይበል:
"ሱብሓነከ አልላሁምመ ረበና ወ ቢሐምዲከ ወተባረከ ኢስሙከ ወተዓላ ጀዱከ ወላኢላሃ ገይሩክ" ትርጉሙ፦ "ጥራት ይገባህ አላህ ሆይ! ምስጋናም ላንተ ነው። ስምህ ከፍ ያለ ግርማህም የላቀ ነው፤ ካንተም በቀር አምላክ የለም።"
6- ከዚያም እንዲህ በማለት በአላህ ይጠበቅ፦ "አዑዙ ቢላሂ ሚነ ሸይጧኒ-ር-ሯጂም" ትርጉሙ፦ "ከተረገመው ሰይጣን በአላህ እጠበቃለሁ።" 7- ከዚያም ቢስሚላህ ካለ በኋላ ፋቲሓን እንዲህ ብሎ ያንብብ፦ «ቢስሚልላሂ‐ር‐ረሕማኒ‐ር‐ረሒም» [ትርጉሙ፡ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው] (1) «አልሓምዱ ሊልላሂ ረቢል ዓለሚን» (ትርጉሙ: ምስጋና ለዓለማት ጌታ ለአላህ የተገባው ነው) (2) «አርረሕማን አርረሒም» (ትርጉሙም: እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው) (3) «ማሊኪ የውሚ-ድ-ዲን» (ትርጉሙ: የፍርዱ ቀን ባለቤት ለሆነው።) (4) «ኢይያከ ነዕቡዱ ወኢይያከ ነሰተዒን» (ትርጉሙ: አንተን ብቻ እንገዛለን አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምንሃለን) (5) «ኢህዲና‐ስ‐ሲሯጦል ሙስተቂም» (ትርጉሙም: ቀጥተኛውን መንገድ ምራን) (6) «ሲሯጦ‐ል‐ለዚነ አንዓምተ ዓለይሂም ገይሪል መግዱቢ ዓለይሂም ወለድ-ዷሊን» (ትርጉሙም: የእነዚያ ፀጋህን የዋልክላቸውን ሰዎች መንገድ በነዚያ የተቆጣህባቸውን እና የተሳሳቱትንም አይደሉም።) (7) [አል'ፋቲሓ፡ 1-7]
ከዚያም «አሚን» ይበል፤ ትርጉሙም አላህ ሆይ! ዱዓችንን ተቀበለን ማለት ነው።
8 - ከዚያም የገራለትን ቁርአን ይቅራ፤ የሱብሒን ሰላት ቁርኣን ንባብ ማርዘሙ መልካም ነው።
9 - ከዚያም ሩኩዕ ያደርጋል፡ ማለትም አላህን በማላቅ ይጎነበሳል። ወደ ሩኩዕ ሲወርድም ሁለት እጆቹን በትከሻው ትይዩ አድርጎ "አሏሁ አክበር" እያለ ይወርዳል። የአኳኋኑ ሁኔታ ሱና፦ ጀርባውን ለጥ አድርጎ ጭንቅላቱንም በጀርባው ልክ አስተካክሎ የሁለት እጆቹ ጣቶችን ለያይቶ ጉልበቱን መያዝ ነው።
10 - በሩኩዑ ጊዜ ሶስት ጊዜ እንዲህ ይበል፡ "ሱብሓነ ረቢየል ዓዚም" (ትርጉሙም፡ ጥራት ይገባህ ታላቁ ጌታየ)፤ "ሱብሓነከሏሁመ ወቢሓምዲከ አሏሁግፊርሊ" (ትርጉሙም፡ ጥራት ይገባህ ምስጋናም ላንተው ነው፤ መሀርታህን ለግሰኝ።) ቢል በላጭ ነው።
11 - ከዚያም ከሩኩዕ ሁለት እጆቹን በትከሻው ትይዩ አድርጎ እንዲህ እያለ ቀና ይበል፡ "ሰሚዐልላሁ ሊመን ሐሚደህ" (ትርጉሙም፡ አላህ የሚያመሰግኑትን ሰሚ ነው።) ኢማሙን ተከትሎ የሚሰግድ "ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ" ሳይሆን "ረበና ወለከል ሓምድ" (ትርጉሙም፡ ጌታችን ሆይ! ምስጋናም ላንተ ነው።) ነው የሚለው።
12 - ከዚያም ቀና ካለ በኋላ እንዲህ ይበል፡ "ረበና ወለከል ሐምድ ሚልኡ ሰማዋቲ ወል አርዲ ወሚልኡ ማሺእተ ሚን ሸይኢን ባዕዱ" (ትርጉሙም፡ ጌታችን ሆይ! ምስጋና በሰማያትና በምድር ሙሉ ላንተ ይሁን፤ ከዚያም በኋላ አንተ በምትሻው ነገር ሙሉም ላንተ ይሁን።)
13 - ከዚያም ለመጀመርያው ሱጁድ እንዲህ እያለ ይወርዳል፡ "አሏሁ አክበር"፤ ሱጁድ የሚያደርገውም በሰባት የሱጁድ አካላቱ ሲሆን እነርሱም፡ ግንባር አፍንጫን ጨምሮ ፣ ሁለት መዳፎች፣ ሁለት ጉልበቶቹ እና የእግር ጫፎች ናቸው። አካላቱን ከጎኑ ያርቃቸው፤ ክርኖቹንም ምድር ላይ አያንጥፋቸው፤ በእግሩ ጫፍም (በጣቶቹ) ወደ ቂብላ ይቅጣጭ።
14 - በሱጁዱም ወቅት ሶስት ጊዜ እንዲህ ይበል፦ "ሱብሓነ ረቢየል አዕላ" (ትርጉሙም፡ ከፍ ያልከው ጌታየ ሆይ! ጥራት ይገባህ።) እንዲህ ብሎ ቢጨምር ደግሞ ይበልጥ የተሻለ ነው፡ "ሱብሓነከሏሁምመ ረብበና ወቢሓምዲከ አሏሁምመግፊርሊ" (ትርጉሙም፡ ጥራት ይገባህ ምስጋናም ላንተ ነው ጌታየ! መሀርታህን ለግሰኝ።)
15 - ከዚያም ከሱጁድ "አሏሁ አክበር" እያለ ቀና ይበል።
16 - ከዚያም በሁለቱ ሱጁዶች መካከል የቀኝ እግሩን ተረከዝ ተክሎ በግራ እግሩ የውስጠኛው ክፍል ላይ ይቀመጥ። የቀኝ እጁን በቀኝ ታፋው ላይ አድርጎ ወደ ጉልበቶቹ አስጠግቶ ያስቀምጣቸው። ትንሿን ጣቱንና የቀለበት ጣቱን አጥፎ ጠቋሚ ጣቱን በዱዓእ ጊዜ ያንቀሳቅስ። የአውራ ጣቱን ጫፍም ከመሀል ጣቱ ጫፍ ጋር አድርጎ እንደ ክብ ነገር ይስራባቸው። የግራ እጁን ደግሞ ጣቶቹን ዘርግቶ በግራ ታፋው ላይ ወደ ጉልበቱ አስጠግቶ ያስቀምጠው።
17 - በሁለቱ ሱጁዶች መካከል ሲቀመጥ እንዲህ ይበል፦ “ረቢግፊርሊ ወርሐምኒ ወህዲኒ ወርዙቅኒ ወጅቡርኒ ወዓፊኒ” ትርጉሙ፡ "አላህ ሆይ ይቅር በለኝ ማረኝ ምራኝ ፣ ደግፈኝ ፣ ጠብቀኝ፣ ስጠኝ፣ ከፍም አድርገኝ።"
18 - ሁለተኛውንም ሱጁድ ንግግሩንም ተግባሩንም ተመሳሳይ በሆነ መልኩ ልክ እንደመጀመርያው ያድርግ። ወደ ሱጁድ በሚወርድበትም ጊዜ "አሏሁ አክበር" ይበል።
19 - ከዚያም ከሁለተኛው ሱጁድ "አሏሁ አክበር" እያለ ቀና ይበል። የሁለተኛውንም ረከዓህ ንግግሩንም ተግባሩንም ልክ በመጀመርያው ረከዓህ እንዳደረገው ያድርግ። ነገር ግን የመክፈቻ ዱዓ አያደርግም።
20 - ከዚያም ሁለተኛውንም ረከዓህ እንዳጠናቀቀ "አሏሁ አክበር" እያለ ቀና ይበልና በሁለቱ ሱጁዶች መካከል እንደተቀመጠው ሆኖ ይቀመጥ።
21 - በዚሁ በተቀመጠበት በሚከተለው መልኩ ተሸሁድን ያነባል፡ “አትተሒያቱ ሊላሂ ወስሶላዋቱ ወጥጠይባቱ ፣ አስሰላሙ ዐለይከ አይዩሀን-ነቢይዩ ወረሕመቱልላሂ ወበረካትሁ ፤ አስሰላሙ ዐለይና ወዓላ ዒባዲላሂ አስሷሊሒነ ፣ አሽሀዱ አንላኢላሀ ኢልለልላህ ወአሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉሁ። አልላሁምመ ሰልሊ ዐላ ሙሐመዲን ወዐላ ኣሊ ሙሐመዲን ከማ ሶልለይተ ዐላ ኢብራሂመ ወዐላ ኣሊ ኢብራሂመ ኢንነከ ሐሚዱን መጂድ። አልላሁምመ ባሪክ ዓላ ሙሐመዲን ወዐላ አሊ ሙሐመዲን ከማ ባረክተ ዐላ ኢብራሂመ ወዓላ አሊ ኢብራሂመ ኢንነከ ሐሚዱን መጂድ። አሏሁማ ኢኒ አዑዙ ቢከ ሚን ዐዛቢል-ቀብሪ ወሚን ዐዛቢ ጀሀነም ወ ሚን ፊቲነቲል-መሕያ ወል-መማቲ ወ ሚን ሸር-ሪ ፊቲናቲል መሲሒ-ድ-ደጃል” ትርጉም ፡- “ክብርና ልዕልና እንዲሁም ሶላቶችና መልካም ነገሮች ሁሉ ለአላህ ናቸው። አንቱ ነቢዩ ሆይ! የአላህ ሰላም፣ እዝነቱና በረከቶች በእርሶ ላይ ይስፈን ፤ ሰላም በእኛና በአላህ ደጋግ ባሮችም ላይ ይስፈን ፤ ከአላህ ሌላ በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ ፤ ሙሐመድም የአላህ አገልጋይና መልዕክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ፤ አላህ ሆይ! ውዳሴህን ለኢብራሂምና ለቤተሰቦቻቸው እንዳወረድክላቸው ሁሉ ለሙሐመድና ለቤተሰቦቻቸው አውርድላቸው፤ አንተ ምስጉንና ኋያል (የላቅክ) ነህና።አላህ ሆይ! ለኢብራሂምና ለቤተሰቦቻቸው ረድዔትን እንዳወረድክላቸው ሁሉ ለሙሐመድና ለቤተሰቦቻቸውም ረድዔትን አውርድላቸው። አንተ ምስጉንና ኋያል (የላቅክ) ነህና። አላህ ሆይ! ከቀብር ፈተና፣ ከጀሀነም ፈተና፣ ከህይወትና ሞት ፈተናዎች እንዲሁም ከመሲሒ ደጃልም ፈተና ክፋት በአንተ እጠበቃለሁ።" ከዚያም ከቅርቢቱ ዓለምና ከመጨረሻው ዓለም የፈለገውን መልካም ነገር በዱዓእ አላህን ይማፀናል።
22 - ከዚያም ወደ ቀኝ እየዞረ እንዲህ ብሎ ያሰላምት "አሰላሙ ዓለይኩም ወራሕመቱሏህ"፤ ወደ ግራ እየዞረም እንዲሁ ይበል።
23 - ሶላቱ ሶስት ረከዓ ወይም አራት ረከዓህ የሚሰገድበት ከሆነ ደግሞ ተሸሁድ ማለትም "አሽሀዱ አን ላ ኢላሃ ኢለሏህ ወአሽሀዱ አነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ" የሚለው ድረስ ካለ በኋላ የቀረውን ረከዓ ለመቀጠል ይቆማል።
24 - ከዚያም "አሏሁ አክበር" እያለ ይቁም እጆቹንም በትከሻው ትይዩ ከፍ ያድርጋቸው።
25 - ከዚያም ሁለተኛውን ረከዓህ በሰገደበት አኳኋን አድርጎ ሶላቱን ይቀጥል፤ ይሁን እንጂ የሚቀራው ቁርአን ፋቲሓን ብቻ ነው።
26 - ከዚያም ተወሩክ በሚባለው አኳኋኑም የቀኝ እግሩን ተረከዝ ተክሎ የግራ እግሩን ተረከዝ ደግሞ በተከለው የቀኝ እግሩ ተረከዝ ስር አሾልኮ መቀመጫውን መሬቱ ላይ ያደርጋል። እጆቹን ደግሞ ልክ በመጀመርያው ተሸሁድ ላይ እንዳደረገው አድርጎ በታፋዎቹ ላይ ያስቀመጣቸዋል።
27 - በዚሁ መቀመጡ ላይ ሙሉ ተሸሁድን ነው የሚቀራው።
28 - ከዚያም ወደ ቀኝ እየዞረ እንዲህ ብሎ ያሰላምት "አሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱሏህ"፤ ወደ ግራ እየዞረም እንዲሁ ይበል።

መልስ - ሶስት ጊዜ "አስተግፊሩሏህ" ካለ በኋላ
- "አሏሁምመ አንተስ-ሰላም ወሚንከስ-ሰላም ተባረክተ ያ ዘል-ጀላሊ ወል-ኢክራም" (ትርጉሙም፡
አላህ ሆይ! አንተ "አስ-ሰላም" ነህ። ሰላምም ከአንተው ነው የሚመጣው። የግርማና የልቅና ባለቤት የሆንከው ጌታየ ሆይ ክብርህ ይስፋ።)

- "ላ ኢላሀ ኢለላህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ፡ ለሁል-ሙልኩ ወለሁል-ሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር አሏሁመ ላ ማኒዐ ሊማ አዕጦይተ ወላ ሙዕጢየ ሊማ መናዕተ ወላ የንፈዑ ዘል-ጀዲ ሚንከል-ጀድ"
(ትርጉሙም፡ ከአላህ በስተቀር በእውነት አምልኮ የሚገባው አምላክ የለም፤ ተጋሪ የለውም። ንግሥናም ምስጋናም የእርሱ ብቻ ነው። እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው። አላህ ሆይ! አንተ የሰጠኸውን የሚያቅበው የለም። የከለከልከውንም ማንም ሊሰጥ አይችልም። እድለኝነትም ሊጠቅም አይችልም። እድለኝነትም ካንተው ነው።)
- "ላ ኢላሀ ኢለላህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ፡ ለሁል-ሙልኩ ወለሁል-ሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር ላ ሓውላ ወላ ቁወተን ኢላ ቢላህ ላ ኢላሀ ኢለሏህ ወላ ነዕቡዱ ኢላ ኢያህ ለሁን-ኒዕመቱ ወለሁል-ፈድሉ ወለሁሥ-ሠናኡል ሐሰን ላ ኢላሀ ኢለላህ ሙኽሊሲነ ለሁድ-ዲን ወለው ከሪሀል-ካፊሩን"
(ትርጉሙም፡ ከአላህ በስተቀር በእውነት አምልኮ የሚገባው አምላክ የለም፤ ተጋሪ የለውም። ንግሥናም ምስጋናም የእርሱ ብቻ ነው። እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው። ከአላህ በስተቀር ምንም ሃይልም ብልሀትም የለም። ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም። ከርሱም ሌላ አንገዛም። ችሮታው የርሱ ብቻ ነው። ውዳሴም ለእርሱ ብቻ ነው። ከአላህ በስተቀር ሌላ በእውነት አምልኮ የሚገባ አምላክ የለም። ከሓዲዎች ቢጠሉም (እኛ) ሃይማኖታችንን በኢኽላስ ለርሱ ያጠራን ነን።)
- "ሱብሐነላህ" (ትርጉሙም፡ አላህ ጥራት ይገባው) ሰላሳ ሶስት ጊዜ፤
- "አልሐምዱሊህ" (ትርጉሙም፡ ምስጋና ሁሉ ለአላህ የተገባ ነው) ሰላሳ ሶስት ጊዜ፤
- "አላሁ አክበር" (ትርጉሙም፡ አላህ የላቀ ነው) ሰላሳ ሶስት ጊዜ፤
ከዚያም እንዲህ ብሎ መቶ ይሞላል፦ - "ላ ኢላሀ ኢለላህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ፡ ለሁል-ሙልኩ ወለሁል-ሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር"
(ትርጉሙም፡ ከአላህ በስተቀር በእውነት አምልኮ የሚገባው አምላክ የለም፤ ተጋሪ የለውም። ንግሥናም ምስጋናም የእርሱ ብቻ ነው። እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው።)
- ሱረቱ አል-ኢኽላስን እና ሱረቱል ፈለቅን ("ቁል አዑዙ ቢረቢል ፈለቅ") እና ሱረቱ-ን-ናስን (“ቁል አዑዙ ቢረቢ-ን-ናስ”) ከፈጅርና ከመግሪብ ሰላት በኋላ ሶስት ሶስት ጊዜ ከሌሎቹ ሶላቶች በኋላ ደግሞ አንድ አንድ ጊዜ መቅራት፤
አየተል ኩርሲይን አንድ ግዜ መቅራት፤

መልስ - ከፈጅር ሰላት በፊት ሁለት ረከዓዎች፤
ከዝሁር ሰላት በፊት አራት ረከዓዎች፤
ከዝሁር ሰላት በኋላ ሁለት ረከዓዎች፤
ከመግሪብ ሰላት በኋላ ሁለት ረከዓዎች፤
ከዒሻ ሰላት በኋላ ሁለት ረከዓዎች፤
ትሩፋቱን በተመለከተ ነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ “በቀንና በሌሊቱ ክፍል አስራ ሁለት ረከዓዎችን ለሰገደ አላህ በጀነት ውስጥ ቤት ይገነባለታል።” ሙስሊም እና አሕመድ እንዲሁም ሌሎችም ዘግበውታል።

መልስ - ጁሙዓ ቀን ነው። ነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "ከቀኖቻችሁ በላጩ ጁምዓ ነው። በዚህ ቀን አደም ተፈጠረ፤ በዚህ ቀንም ሞተ፤ በዚህ ቀን ነው የመጨረሻው ቀንድ የሚነፋው፤ በዚህ ቀን ነው በድንጋጤ መሞት የሚከሰተው። በዚያ ቀን በኔ ላይ ሶለዋት አብዙ፤ ምክንያቱም ሶለዋታችሁ ለኔ ይቀርብልኛልና።" "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! አፈር በልቶዎት ሳለ ሰለዋታችን እንዴት ይቀርብሎታል?" አሏቸው፤ እርሳቸውም፦ "አላህ ምድርን የነቢያትን ሥጋ ከመብላት ከልክሏታል።" አቡ ዳውድና ሌሎችም ዘግበውታል።

ሐ- በእያንዳንዱ ለአቅመ አዳም የደረሰ ጤነኛ አእምሮ ያለው መንገደኛ ያልሆነ ወንድ ሙስሊም ላይ ሁሉ በነፍስ ወከፍ ግዴታው ነው።
የላቀዉ አላህ እንዲህ ብሏል፦ {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በዐርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ። መሸጥንም ተዉ። ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነወ። 9} [ሱረቱል ሙናፊቁን፡ 9]

መልስ - የጁምአ ሰላት ረከዓዎች ብዛት ኢማሙ ጮክ ብለው የሚቀሩባቸው ሁለት ረከዓዎች ሲሆኑ ከሰላት በፊትም ሁለት የታወቁ ኹጥባዎች አሉት።

ሐ - በሸሪዓዊ ዑዝር ካልሆነ በቀር ከጁምዓ ሰላት መቅረት የሚፈቀድ አይደለም። ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡- "በስንፍና ሶስት ጁምዓዎችን ያሳለፈ ሰው አላህ በልቦናው ላይ ያትምበታል።" አቡ ዳውድና ሌሎችም ዘግበውታል።

መልስ-
1 - ገላን መታጠብ፤
2 - ሽቶ መቀባት፤
3 - የክት (መልካም) ልብስን መልበስ፤
4 - ወደ መስጅድ ቀደም ብሎ መሄድ፤
5 - በነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ላይ ሶለዋት ማብዛት፤
6 - ሱረቱል ከህፍን መቅራት፤
7 - ወደ መስጅድ በእግር መሄድ፤
8- ዱዓእ ተቀባይነት የሚያገኝበትን ሰዓት መጠባበቅ፤

መልስ - ከዐብደ፤አህ ኢብኑ ዑመር ረዲየሏሁ ዓንሁ በተላለፈ ሐዲሥ የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "በጀምዓ የሚሰገድ ሰላት ለብቻ ከሚሰገድ ሰላት በሃያ ሰባት እጥፍ ይበልጣል።" ሙስሊም ዘግበውታል።

መልስ - በሰላት ሰአት ልቦና የተጣደ መሆኑ እና አካልም መስከኑ ነው።
የላቀዉ አላህ እንዲህ ብሏል፦ {ምእምናን ፍላጎታቸውን ሁሉ በእርግጥ አገኙ (ዳኑ)። 1} {እነዚያ እነርሱ በስግደታቸው ውስጥ (አላህን) ፈሪዎች። 2} [ሱረቱ አል-ሙእሚኑን፡ 1፣2]

ሐ - በተወሰነ የጊዜ ገደብ ውስጥ ለተወሰኑ የማህበረሰብ ክፍሎች የሚሰጥ የገንዘብ ግዴታ ነው።
ከእስልምና መሰረቶች መካከል አንዱ ሲሆን ከሀብታሞች ተወስዶ ለድሆች የሚሰጥ የግዴታ ምጽዋት ነው።
የላቀዉ አላህ እንዲህ ብሏል፦ "ዘካንም ስጡ።" [ሱረቱል በቀራህ፡ 43]

መልስ - ከዘካ ውጭ የሆነ በማንኛውም ጊዜ በበጎነት የሚደረግ መርዳትን መሰል ምጽዋትን የሚያጠቃልል ነው።
የላቀዉ አላህ እንዲህ ብሏል፦ {በአላህም መንገድ ለግሱ።} [ሱረቱል በቀራህ፡ 195]

ሐ- አላህን ማምለክን በማሰብ ጎህ ከሚቀድበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ጀንበር መጥለቅ ድረስ ጾምን ከሚያፈርሱ ነገሮች በመታቀብ አላህን ማምለክ ነው። ሁለት ዓይነትም ነው፦
የግዴታ ጾም፡- ከእስልምና ምሰሶዎች አንዱ የሆነውን የረመዷንን ወር መጾምን ይመስል።
የላቀዉ አላህ እንዲህ ብሏል፦ {እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ እንደ ተጻፈ በናንተም ላይ ተጻፈ (ተደነባ) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና። 183} [ሱረቱል በቀራህ፡ 183]
ግዴታ ያልሆነ ጾም፡- በየሳምንቱ ሰኞ እና ሐሙስ መጾም እና ከየወሩ ሦስት ቀናትን መጾምን የመሳሰሉ ጾሞችን የሚመለከት ሲሆን ከእንዲህ ዓይነቶቹ በላጩ አያመል ቢድ የሚባሉት (በሒጅሪ አቆጣጠር የወሩን 13ኛ፣ 14ኛውና 15ኛውን) ቀናት መጾም ነው።

መልስ- አቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፡- "የረመዷንን ወር በእምነት እና ምንዳውን ከአላህ ለማግኘት በማሰብ የጾመ ሰው ያለፈው ኃጢአቱ ይሰረይለታል።" ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

መልስ - አቡ ሰዒድ አል-ኹድሪይ አላህ ይውደድላቸውና ባስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፡- "ማንኛውም ባርያ በአላህ መንገድ አንድ ቀን ቢፆም አላህ ፊቱን ከጀሀነም የሰባ ክረምት ያህል ያርቅለታል።" ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
- "ሰባ ክረምት" ሲባል ሰባ ዓመት እንደማለት ነው።

መልስ-1- ሆን ብሎ መብላትና መጠጣት፤
2- ሆን ብሎ ማስታወክ፤
3- ከእስልምና መቀልበስ (ካፊር መሆን)

መልስ-1- ፊጥራን ማፋጠን፤
2- ሰሑር ማዘግየት፤
3- በጎ ስራን እና ዒባዳን ማብዛት፤
4- ፆመኛ ሆኖ ሲዘልፉት "እኔ ፆመኛ ነኝ" ማለት
5- ፆም በሚፈቱበት ጊዜ ዱዓእ ማድረግ፤
6- ጾምን በእርጥብ ቴምር ወይም በማንኛውም ቴምር ማፍጠር፤ ካልተገኘ ደግሞ በውኋ ማፍጠር፤

መልስ - ሐጅ ማለት፡- የተወሰነ የአምልኮ ስርአትን፤ በተወሰነ ወቅት ላይ ለማከናወን ወደ ተከበረው የአላህ ቤት ሄዶ አላህን ማምለክ ነው።
የላቀዉ አላህ እንዲህ ብሏል፦ {ለአላህም በሰዎች ላይ ወደርሱ መኼድን በቻለ ሁሉ ላይ ቤቱን መጎብኘት ግዴታ አለባቸው። የካደም ሰው አላህ ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ነው። 97} [ሱረቱ ኣሊ-ዒምራን፡ 97]

መልስ-1- ኢሕራም፤
2- በዐረፋ ላይ መቆም፤
3- ጠዋፍ አል-ኢፋዷ፤
4- በሰፋ እና መርዋ መካከል መመላለስ፤

መልስ- ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው "የአላህ መልእክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ" ብለው፡- "(ከሚስቱም ጋር) ግንኙነት ሳይፈፅም ኀጢአትንም ሳይሠራ ከሓጅ የተመለሰ ሰው ልክ እናቱ በወለደችበት ቀን እንደነበረው ሆኖ ይመልለሳል።" ቡኻሪይ እና ሌሎችም ዘግበውታል።
- "ልክ እናቱ በወለደችበት ቀን እንደነበረው ሆኖ ይመልለሳል።" ሲባል ከኃጢአት የጸዳ ሆኖ ማለት ነው።

መልስ - ዑምራ ማለት፡- በየተኛውም ወቅት የተወሰነ የአምልኮ ስርአትን ለማከናወን ወደ ተከበረው የአላህ ቤት ሄዶ አላህን ማምለክ ነው።

መልስ-1- ኢሕራም፤
2 - ጠዋፍ ማድረግ፤
3 - በሰፋ እና መርዋ መካከል መመላለስ፤

መልስ - እስልምናን በማስፋፋት እና ከእስልምና እና ከሙስሊሞችም በመከላከል ረገድ ያቅምን ማድረግ ወይም የእስልምና እና የሙስሊሞችን ጠላቶች መፋለም ነው።
የላቀዉ አላህ እንዲህ ብሏል፦ {ቀላሎችም ከባዶችም ሆናችሁ ዝመቱ። በአላህም መንገድ በገንዘቦቻችሁ በነፍሶቻችሁም ታገሉ። ይህ የምታውቁ ብትሆኑ ለናንተ በጣም የተሻለ ነው። 41} (ሱረቱ-ተውባህ፡ 41)