የኢስላማዊ ስርአት ክፍል

መልስ- 1- ጥራት ይገባውና የላቀው አላህን ማላቅ፤
2- ተጋሪ ሳያደርጉ እርሱን በብቸኝነት ማምለክ፤
3- እርሱኑ መታዘዝ፤
4- አለማመፅ፤
5- ለቁጥር የሚያታክት ለሆነው ችሮታውና ፀጋው ማመስገንና ተገቢውን ሹክር ማድረስ፤
6- ቀድሞ ለወሰነው ዕጣ ፈንታ መታገስ፤

መልስ-1- እርሳቸውን መከተል እና እንደ አርአያ አድርጎ መያዝ፤
2- እርሳቸውን መታዘዝ
3- እርሳቸውን አለማመፅ
4- የተናገሩትን አምኖ መቀበል፤
5- በሱናቸዉ ላይ አዲስ ፈሊጥ አለማምጣት፤
6- እሳቸውን ከራስም ከሰውም ሁሉ በላይ አስበልጦ መውደድ፤
7- እሳቸውን ማክበር፣ ማገዝና ሱናቸውን መርዳት፤

መልስ - 1 - አላህን በማመፅ ላይ እስካልሆነ ድረስ ወላጆችን መታዘዝ፤
2- ወላጆችን መኸደም (መንከባከብ)
3 - ወላጆችን ማገዝ፤
4- የወላጆችን ጉዳይ ማሳካት፤
5- ለወላጆች ዱዓእ ማድረግ፤
6- ከእነርሱ ጋር ሲጫወቱ ስርአትን መጠበቅ ይገባል፤ በዚህም መሰረት ከንግግሮች ትንሽ የሆነው “ኡፍ” ማለት እንኳ አይፈቀድም።
7- ለወላጆች የፈገግታ ፊትን ማሳየት ለነርሱ ፊትን አለማጨፍገግ፤
8 - ድምፄን ከወላጆቼ ድምጽ በላይ ከፍ አላደርግም፤ በጥሞና አዳምጣቸዋለሁኝም፤ በንግግራቸው መሀል አላቋረጣቸውምም፤ በስማቸው ነጥየም አልጠራቸውም፤ ይልቁን “አባየ!”
“እማየ!” ነው የምላቸው።
9- አባትና እናቴ ክፍል ውስጥ እያሉ ከመግባቴ በፊት ፈቃዳቸውን እጠይቃለሁ፤
10- የወላጆቻችንን እጆችና ግንባራቸውን መሳም።

መልስ - 1 - ወንድምንም እህትንም አጎትንም አክስትንም ሌሎች ዘመዶችንም በመዘየር፤
2- ለነርሱ በንግግርም ሆነ በተግባር ደግ መሆንና እነርሱንም በመርዳት፤
3- እነርሱን ማግኘትና ሁኔታቸውንም መጠየቅ፤

መልስ-1 - የምወዳጀውም የምጎዳኘውም ጥሩ ሰዎች ጋር ነው፤
2- ከክፉ ሰዎች ጋር ከመጎዳኘትም እርቃለሁ፤
3- ወንድሞቼ ጋር ሰላምታን እለዋወጣለሁ እጨባበጣለሁም፤
4- ከታመሙም እጠይቃቸዋለሁ፤ አላህ እንዲያሽራቸውም ዱዓእ አደርግላቸዋለሁ፤
5- ሲያስነጥሱ "የርሐሙከላህ" ብዬ ዱዓእ አደርግላቸዋለሁ፤
6- እንድጎበኛቸው ከጠሩኝም ግብዣቸውን እቀበላለሁ፤
7- ምክር እለግሳቸዋለሁ፤
8- ሲበደሉ እረዳቸዋለሁ፤ ሲበድሉም አቅባቸዋለሁ፤
10- ለራሴ የምወደውን ለሙስሊም ወንድሜም እወድለታለሁ፤
11- እርዳታዬን ሲያስፈልጋቸውም እረዳቸዋለሁ፤
12- በቃልም ሆነ በተግባር ምንም አላስቸግራቸውም፤
13 - ምስጢራቸውን እጠብቃለሁ፤
14- አልሰድባቸው፣ አላማቸው፣ አልንቃቸው፣ አልመቀኛቸው፣ አልሰልላቸው፣ አላታልላቸውም።

መልስ-1- ጎረቤቴን በቃልም ሆነ በተግባር በጎ አደርግለታለሁ፤ እርዳታዬ ሲያስፈልገውም እረዳዋለሁ።
2- በበዓል፣ በትዳር ወይም በሌላ ምክንያት የደስታ ቀን ካለው እንኳን ደስ አለህ እለዋለሁ፤
3- ከታመመ እጠይቀዋለሁ፤ ከተጎዳም አጽናናዋለሁ፤
4- ከምሰራው ምግብ በተቻለኝ መጠን አቋድሰዋለሁ፤
5- በቃልም ሆነ በድርጊት አላስቸግረውም፤
6- በመሰለል ወይም በሚያስቸግር ድምፅ አልረብሸውም፤ እታገሰዋለሁኝም።

መልስ-1- በእንግድነት ለጋበዘኝ እቀበለዋለሁ፤
2- አንድን ሰው መጎብኘት ከፈለግኩኝም ፈቃዳቸውን ጠይቄ ቀጠሮ እይዛለሁ፤
3- ከመግባቴ በፊትም ፈቃድ እጠይቃለሁ፤
4- ለጉብኝቴ አልዘገይም፤
5- የቤቱ አባላት ላይ ከማፍጠጥ ዐይኔን እገድባለሁ፤
6- እንግድነት ሲመጣብኝም ፈገግታ በተሞላበት ፊት እና በጥሩ የአቀባበል ቃላት መርጬ ባማረ መልኩ እቀበላለሁ፤
7- እንግዳየንም በተሻለ ቦታ ላይ እንዲቀመጥ አደርጋለሁ፤
8- የሚበላና የሚጠጣ ነገር እንዲቋደስ አድርጌ አስተናግዳለሁ፤

መልስ-1- ህመም ከተሰማኝ ቀኝ እጄን በሚያመኝ ስፍራ ላይ አድርጌ ሶስት ጊዜ "ቢስሚላህ" ካልኩ በኋላ ሰባት ጊዜ እንዲህ እላለሁ "አዑዙ ቢዒዘቲላሂ ወቁድረቲሂ ሚን ሸሪ ማ አጂዱ ወኡሓዚሩ" (ትርጉሙም: ከማገኘው ክፋት በአላህ ክብር እና ሀይል እጠበቃለሁ እና እጠነቀቃለሁ።"
2- አላህ በወሰነው ነገር ወድጄ እታገሳለሁ፤
3- የታመመ ወንድሜን ለመጠየቅ እሯሯጣለሁ ዱዓእም አደርግለታለሁ፤ እርሱ ዘንድ ግን አብዝቼ አልቀመጥም።
4- ገና ሳይጠይቀኝ ሩቃ አደርግለታለሁ፤
5- በሚችለው መጠን እንዲታገስ፣ ዱዓእ እንዲያደርግ፣ ሶላቱንም እንዲሰግድና በቻለው ልክ ንፅህናውንም እንዲጠብቅ እመክረዋለሁ፤
6- ለህመምተኛ የሚደረገው ዱዓእ ሰባት ጊዜ እንዲህ ማለት ነው፡- "አስአሉ አላሀ አልዐዚም ረበ አልዐርሺል አልዐዚም አን የሽፊየከ" (ትርጉሙም: ታላቅ የሆነውን እና የዐርሽ ጌታ የሆነውን አላህ እንዲያሽርህ እለምነዋለሁ።"

መልስ-1- ኒያን ለልዕለ ኋያሉ አላህ ብቻ ብሎ ጥርት ማድረግ፤
2- የተማርኩትን እውቀት እተገብራለሁ፤
3- ኡስታዜን (አስተማሪየን) በፊታቸውም በሌሉበትም አከብራቸዋለሁ፤
4- ከፊት ለፊታቸው ስቀመጥም ስርአት ተላብሼ እቀመጣለሁ፤
5- በጥሞና አዳምጣቸዋለሁ በሚያስተምሩኝ ጊዜም አላቋርጣቸውም፤
6- ጥያቄ ካለኝም ጨዋነትን በተላበሰ መልኩ እጠይቃለሁ፤
7- ስጠራቸውም በስማቸው ነጥየ አልጠራቸውም።

መልስ-1- በአብሮነት የተቀማመጡትን ሰዎች ሰላም እላለሁ፤
2 - በአብሮነት ከተቀማመጡት ሰዎች ጫፍ ላይ ባገኘሁት ክፍት ቦታ እቀመጣለሁ፤ ማንንም ከተቀመጠበት አላስነሳም፤ በሁለት ሰዎች መካከል የምቀመጠውም ከፈቀዱልኝ ብቻ ነው፤
3- አቀማመጤንም ሌላም ሰው ለመቀመጥ እንዲችል አድርጌ አሰፋለሁ፤
4- ተቀማማጮቹን በንግግራቸው መሀል አላቋርጣቸውም፤
5- ከተቀመጡት ሰዎች መካከል መሄድ ካለብኝም ከመሄዴ በፊት አስፈቅዳቸዋለሁ፤
6- አብሮ የመቀማመጣችን ጊዜው ካለቀም (የሚከተለውን) የመቀማመጥ ከፋራ ዱዓእ አደርጋለሁ: "ሱብሓነከሏሁመ ወቢሓምዲከ አሽሀዱ አን ላ ኢላሃ ኢላ አንተ አስተግፊሩከ ወአቱቡ ኢለይክ" (ትርጉሙም: ክብርና ምስጋና ላንተ ይሁን፤ ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለም እመሰክራ ለሁ፤ መሀርታህንም እከጅላለሁ ወደ አንተም ተፀፅቻለሁ።)

መልስ-1 - ቀደም ብዬ እተኛለሁ፤
2 - የምተኛውም ጡሀራ ላይ ሆኘ ነው፤
3- በሆዴ ተደፍቼ አልተኛም፤
4 - ቀኝ እጄንም ከቀኝ ጉንጬ ስር አድርጌ በቀኝ ጎኔ እተኛለሁ፤
5- አልጋዬን አራግፋለሁ፤
6- አየተል-ኩርሲይን፣ ሱረቱል ኢኽላስን እና ከአል-ሙዓዊዘተይንን ሶስት ጊዜ ከቀራሁ በኋላ እንዲህ እላለሁ: 5- "ቢስሚከሏሁመ አሙቱ ወአሕያ" (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! የምኖረውም የምሞተውም በስምህ ነው።)
7- ለፈጅር ሰላት እነቃለሁ፤
8- ከእንቅልፌ በነቃሁም ጊዜ እንዲህ እላለሁ:- "አልሐምዱ ሊላሂ አልለዚ አሕያና በዕደ ማ አማተና ወኢለይሂ ኑሹር" (ትርጉሙም: ምስጋና ከሞትን በኋላ ህያው ላደረገን አላህ የተገባ ነው። መመለሻ ወደርሱው ብቻ ነው።"

መልስ-
1 - በመብላትና በመጠጣቴ ልዕለ ኃያል የሆነው አላህን መታዘዝን ነው የማስበው፤
2- ከመመገቤ በፊት እጄን እታጠባለሁ፤
3- "ቢስሚላህ" ብየ ከመአዱ መሀልም ከሌላ ሰው ፊትም ሳይሆን በፊትለፊቴ ካለው በቀኝ እጄ እበላለሁ፤
4- "ቢስሚላህ" ማለትን ከረሳሁ ባስታወስኩበት ጊዜ እንዲህ እላለሁ "ቢስሚላሂ አወሊሂ ወአኺሪሂ"
5- ከምግቡ የተገኘውን እመገባለሁ፤ ምግቡንም አላነውርም፤ ከወደድኩት እበላዋለሁ ባልወደ እንኳ አላነውረውም፤
6- ጥቂት ጉርሻዎችን እበላለሁ እንጂ አብዝቼ አልመገብም፤
7- ምግብና መጠጥ ላይ አልተነፍስም፤ እስኪቀዘቅዝ ድረስ ማቆየት ካለብኝ አቆየዋለሁ እንጂ፤
8- ማእዱን ከቤተሰብና ከእንግዳ ጋር እጋራለሁ፤
9- ከእኔ ከሚበልጠኝ ሰው ጋር ስቀርብ ቀድሜው መብላት አልጀምርም፤
10- ስጠጣም "ቢስሚላህ" ብየ ተቀምጬ ሦስት ጊዜ ተጎንጭቼ እጠጣለሁ፤
11- በልቼ ስጨርስም አላህን አመሰግናለሁ።

መልስ - 1 - ልብሴን በቀኝ በኩል ጀምሬ እየለበስኩ አላህን አመሰግነዋለሁ፤
2- ልብሴን ከቁርጭምጭሚቴ ወደታች አላረዝምም፤
3- ወንድ ልጆች የሴቶችን ልብስ ሴት ልጆችም የወንዶችን ልብስ አይለብሱም፤
4- ልብሴ የከሀዲዎችንና የኃጢአተኞችን ልብስ አለመምሰል ይጠበቅበታል፤
5- ልብስ በሚይወልቁበት ጊዜ "ቢስሚላህ" ማለት፤
6- ጫማ ሲደረግም መጀመሪያ ላይ በቀኝ በኩል ሲወለቅ ደግሞ በግራ በኩል ነው።

መልስ- "ቢስሚላህ አልሐምዱ ሊላህ" እልና እንዲህ እላለሁ፦ "ሱብሐነ ለዚ ሰኸረ ለና ሀዛ ወማ ኩና ለሁ መቅሪኒን ወኢና ኢላ ረቢና ለሚንቀሊቡን" {«ያ ይህንን የማንችለው ስንሆን ለእኛ ያገራለን ጌታ ጥራት ይገባው። (13) እኛም በእርግጥ ወደ ጌታችን ተመላሾች፤ነን» (እንድትሉ)። 14} [ሱረቱ አዝዙኽሩፍ፡ 13 -14]
2- በሙስሊሞች በኩል ካለፍኩም በኢስላማዊ ሰላምታ አቀርባለሁ፤

መልስ- 1- የምጓዘው ከመንገዱ በቀኝ በኩል ሆኖ በአረማመዴም ልከኛ እና ትሁት ሆኜ ነው፤
2- ካገኘሁት ሰው ጋር ሰላምታ እለዋወጣለሁ፤
3- አይኔንም ዝቅ አደርጋለሁ ማንንም ደግሞ አላስቸግርም፤
4- በመልካም እያዘዝኩ ከመጥፎም እከለክላለሁ፤
5- በመንገድ ላይ የማገኘውንም አስቸጋሪ ነገርን አስወግዳለሁ፤

መልስ- 1- ስወጣም እንዲህ እያልኩ ግራ እግሬን አስቀድሜ ነው፦ "ቢስሚላሂ ተወከልቱ ዐለላሂ ላ ሐውላ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላሂ፤ አልላሁመ ኢኒ አዑዙ ቢከ አን አዲለ አው ኡዶለ አው አዚለ አው ኡዘለ አው አዝሊመ አው ኡዝለመ አው አጅሀለ አው ዩጅሀለ ዐለይ" (ትርጉሙም፡ በአላህ ስም የምመካውም በእርሱው ነው፤ ብልሀትም ይሁን ሀይል በርሱ ብቻ ነው። አላህ ሆይ! ራሴ ከመሳሳት ወይም ሌሎች እንዲሳሳቱ ከማድረግ፤ ከመንዳለጥ ወይም ሌሎች እንዲንዳለጡ ከማድረግ ከመበደል ወይም ሌሎች እንዲበደሉ ከማድረግ፤ ከመጃጃል ወይም ሌሎች እንዲጃጃሉብኝ ከመሆን በአንተው እጠበቃለሁ።) 2- ስገባም እንዲህ እያልኩ ቀኝ እግሬን አስቀድሜ ነው፡ "ቢስሚላሂ ወለጅና ወቢስሚላሂ ኸረጅና ወዐላ ረቢና ተወከልና" (ትርጉሙም፡ በአላህ ስም ገባን በአላህም ስም ወጣን፤ የምንመካውም በአላህ ነው።)
3- ጥርሴን ሲዋክ በማድርግ እጀምርና ከዚያም ለቤተሰብ አባላቱ ሰላምታ እሰጣለሁ፤

መልስ-1- ስገባ ቀኝ እግሬን አስቀድሜ እገባለሁ፤
2- ከመግባቴ በፊትም እንዲህ እላለሁ፡- "ቢስሚላሂ አልላሁማ ኢኒ አዑዙ ቢከ ሚነል-ኩብሢ ወልኸባኢሥ" (ትርጉሙም፡ በአላህ ስም አላህ ሆይ! ከክፉ ወንድም ሆነ ሴት ጂን በአንተ እጠበቃለሁ።)
3- የአላህ ስም የተጠቀሰበትን ነገር ይዤ አልገባም፤
4 - ስፀዳዳም እደበቃለሁ፤
5- በምፀዳዳበት ጊዜ አላወራም፤
6- ሽንትም ይሁን ሰገራ ስፀዳዳ ወደ ቂብላም አልዞርም ጀርባየንም ለቂብላ አልሰጥም፤
7- ነጃሳን ለማስወገድ ግራ እጄን እጠቀማለሁ እንጂ ቀኝ እጄን አልጠቀምም፤
8- ሰዎች በሚጓዙበት መንገድ ወይም ጥላ ስር አልፀዳዳም፤
9- ከተፀዳዳሁ በኋላ እጄን እታጥባለሁ፤
10 - ግራ እግሬን አስቀድሜ እወጣለሁ “ጉፍራነክ” እላለሁ፤

መልስ-1- ወደ መስጂድ ስገባ ቀኝ እግሬን አስቀድሜ እገባለሁ እንዲህም እላለሁ፦ "ቢስሚላህ አልላሁምመ ኢፍተሕሊ አብዋበ ረሕመቲክ" (ትርጉሙም: በአላህ ስም አላህ ሆይ! የእዝነት ደጆችህን ክፈትልኝ።)
2- ሁለት ረከዓ ሳልሰግድ አልቀመጥም፤
3- በሰጋጆች መካከል አላልፍም፤ የጠፋ ነገርንም መስጂድ ውስጥ አላውጅም፤ ወይም መስጂድ ውስጥ አልሸጥ አልገበይም፤
4- ከመስጂድ ስወጣ ግራ እግሬን አስቀድሜ እንዲህ እያልኩ እወጣለሁ፡- "ቢስሚላሂ አልላሁመ ኢኒ አስአሉከ ሚን ፈድሊክ" (ትርጉሙም: በአላህ ስም፤ አላህ ሆይ! ከችሮታህ እንድትለግሰኝ እማፀንሀለሁ።)

መልስ 1 - ሙስሊም የሆነን ሰው ሳገኝ በእጄ ምልክት በመስጠት ብቻ አልያም በሌላ መልኩ ሳይሆን “አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱህ” በማለት ሰላምታየን እጀምራለሁ።
2- ሰላም ለምለው ሰውም ፊቴን ፈገግ አደርግለታለሁ፤
3- በቀኝ እጄ በመጨባበጥም ሰላምታ እለዋወጣለሁ፤
4- አንድ ሰው ሰላምታ ቢያቀርብልኝ ከርሱ በተሻለ ሰላምታ አልያም አምሳያዋን እመልስለታለሁ፤
5- ለከሀዲ ኢስላማዊ ሰላምታን በመስጠት አልጀምርለትም፤ እርሱ ከጀመረ ደግሞ አምሳያዋን እመልስለታለሁ።
6- ታናሽ ለታላቁ፣ እግረኛው ለሚጋልበው፣ ተቀመጦ ያለው ለሚራመደው፣ ጥቂቶቹ ለብዙዎቹ ሰላምታ ይሰጣጣሉ፤

መልስ-1- ወደ ቦታው ከመግባቴ በፊት ፈቃድ እጠይቃለሁ:
2- ፍቃድ የምጠይቀው ሶስት ጊዜ ሲሆን ከዚያ በላይ ከቆዩብኝ ትቼ እሄዳለሁ፤
3- በር ሳንኳኳ በቀስታ ነው፤ አንኳኩቼ ስቆምም በበሩ ፊት ለፊት ሳይሆን ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ዞር ብዬ ነው የምቆመው፤
4- ወደ አባቴ ወይም ወደ እናቴ አልያም ወደ ማንኛውም ሰው ክፍል ውስጥ ፍቃዳቸውን ሳልጠይቅ አልገባም፤ በተለይም ጊዜው ጎህ ከመቅደዱ በፊት፣ እኩለ ቀን ላይ ከዝሁር ሶላት በፊት (አረፍ በሚሉበት ሰአት) እና ከዒሻ ሶላት በኋላ ከሆነ፤
5- ሰው መኖርያው አድርጎ ያልያዛቸው ቦታዎች ለምሳሌ፡ ሆስፒታል ወይም ሱቅ ከሆነ ግን ፍቃድ ሳልጠይቅም መግባት እችላለሁ፤

መልስ-1- እንስሳውን እመግበዋለሁ አጠጣዋለሁም፤
2- ለእንስሳት ርህራሄ ማሳየት እና ማዘን፤ የማይችሉትን አለማሸከም፤
3- እንስሳትን በምንም አይነት መልኩ ስቃይ ወይም ጉዳት አላደርስባቸውም፤

መልስ-1- በስፖርታዊ እንቅስቃሴ አላህን በመታዘዝ እና ውዴታውን በመፈለግ ላይ መጠናከርን አስብበታለሁ (ኒያ አደርጋለሁ)
2- በሶላት ጊዜ አንጫወትም፤
3- ወንድ ልጆች ከሴት ልጆች ጋር ተቀላቅለው ስፖርታዊ እንቅስቃሴ አያደርጉም፤
4- ገላየን (አውራዬን) የሚሸፍን የስፖርት ትጥቅ እለብሳለሁ፤
5- ከተከለከሉ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እጠነቀቃለሁ፤ ማለትም ፊትን መምታት ወይም ሀፍረተ ገላ (አውራ) መግለጥን ካለባቸው ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እጠነቀቃለሁ፤

መልስ-1- ለቀልድም ቢሆን አለመዋሸት እውነትን በመናገር መቀለድ፤
2- ከማፌዝና ከማላገጥ እንዲሁም ሰዎችን ከመጉዳትና ከማስደንገጥ በፀዱ ቀልዶች መቀለድ፤
3- ቀልድ አለማብዛት፤

መልስ-1- ሲያስነጥሰን እጅን ወይ አንዳች ልብስ ወይም መሀረብ አፍ ላይ ጣል ማድረግ፤
2- ካስነጠሰን በኋላ "አልሐምዱ ሊላህ" በማለት አላህን ማመስገን፤
3- ወንድሙ ወይም ባልንጀራው “የርሐሙከላህ” (ትርጉሙም: አላህ ይዘንልህ) ይበለው፤
እንደዛ ካሉት፡- “የህዲኩሙላሁ ወዩስሊሕ ባለኩም" (ትርጉሙም: አላህ ይምራህ ጉዳይህንም ያስተካክልልህ”
ይበል።

መልስ-1- ማዛጋትን ለማፈን መሞከር፤
2- ሲያፋሽጉ "አህ!" "አህ" የሚለውን የማዛጋት ድምፅ ከፍ ማድረግ አይገባም፤
3- እጅን አፍ ላይ ማድረግ፤

መልስ-- ውዱእ ካደረጉ በኋላ ጡሀራ ሆኖ መቅራት፤
2- ስርአትን ተላብሶ እና በክብር መቀመጥ፤
3- መቅራት ስጀምር አላህ ከሰይጣን እንዲጠብቀኝ (አዑዙ ቢላህ) እላለሁ፤
4- የምቀራውን ቀርአን አስተነትናለሁ።