የነቢዩ ﷺ የህይወት ታሪክ ክፍል

መልስ - እሳቸው የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሙሐመድ ብን ዐብደላህ ቢን ዐብዱል ሙጦሊብ ቢን ሀሺም ናቸው፤ ሀሺም ከቁረይሽ ዘር ነው፤ ቁረይሾችም ከዐረብ ዝርያዎች ናቸው፤ ዐረቦች ደግሞ የኢስማዒል ዘር ሲሆኑ ኢስማዒል ደግሞ የኢብራሂም ዘር ናቸው። በሳቸውም በነብያችንም በላጭ የሆነው የአላህ ሰላዋትና ሰላም ይስፈንባቸውና።

መልስ- አባታቸው የሞተው እርሳቸው የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ገና ሳይወለዱ በእርግዝና ሳሉ ነበር።

መልስ- የዝሆን አመት ተብሎ በተሰየመው አመት በወርሀ ረቢዐል አወል እለተ ሰኞ ነው።

መልስ - የአባታቸው ባሪያ ኡሙ አይመን፤
- የአጎታቸው አቡ ለሀብ ባርያ ሡወይባህ፤
- ሐሊመቱ-ስ-ሰዕዲያህ፤

መልስ - በስድስት ዓመታቸው እናታቸው ስትሞት አያታቸው ዐብዱል ሙጦሊብ ይንከባከቧቸው ጀመር።

መልስ- ስምንት አመት ሲሆናቸው አያታቸው ዐብዱል ሙጦሊብ ሞቱና ተንከባካቢያቸው አጎታቸው አቡ ጧሊብ ሆኑ።

መልስ - ከአጎታቸው ጋር ወደ ሶርያ የሄዱት በአሥራ ሁለት ዓመታቸው ነው።

መልስ - ሁለተኛው ጉዟቸው በኸዲጃ ረዲየሏሁ ዓንሀ ገንዘብ ለመገበያየት ያደረጉት ጉዞ ነበር። እሳቸው የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ከጉዞ ተመልሰውም እድሜያቸው ሃያ አምስት አመት ሆኖ አገቧት።

መልስ - ቁረይሾች ካዕባን እንደገና የገነቡት የሳቸው ዕድሜ ሠላሳ አምስት ሲሆን ነበር።
ሐጀረል አስወድን ማን እንደሚያስቀምጠው በመካከላቸው የሀሳብ ልዪነት በተነሳ ጊዜ እርሳቸውን ፈራጅ አድርገዋቸው ነበር። እርሳቸውም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አንዳች ልብስ አምጥተው ከየጎሳው አንድ አንድ ሰው ተውክሎ የልብሱን ጠርዝ እንዲይዝ አዘዙ። ጎሳዎቹም አራት ነበሩ። የእያንዳንዱ ነገድ ተወካይ ጠርዝ ጠርዙን ይዞ ከፍ እንዳደረገላቸው እሳቸውም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በእጃቸው ተቀብለው ቦታው ላይ አደረጉት።

መልስ - የአርባ ዓመት ጎልማሳ ነበሩ፤ የተላኩትም ለሰዎች ሁሉ አብሳሪና አስጠንቃቂ ተደርገው ነው።

መልስ - መጀመርያ ወሕይ (መለኮታዊ ራዕይ) ሲወርድላቸው የነበረው በእውነተኛ ህልም መልኩ ነበር። ምንም ዓይነት ህልም ቢያዩ ልክ እንደ ንጋት ጎህ ፍንትው ብሎ እውን ይሆን ነበር።

መልስ- በሒራእ ዋሻ ውስጥ አላህን ያመልኩ እና ለዛም ብለው ስንቅም ይቋጥሩ ነበር።
በዋሻው ውስጥ አላህን እያመለኩ በነበረበት ጊዜም ነበር ወሕይ የወረደላቸው።

መልስ- ተከታዩ የላቀው አላህ ቃል ነው፦ {አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም። 1 ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)። 2 አንብብ፤ ጌታህ በጣም ቸር ሲሆን፤ 3 ያ በብዕር ያስተማረ። 4 ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲሆን። 5} [አልዓለቅ፡ 1 - 5]

መልስ - ከወንዶቹ አቡበከር አስ'ሲዲቅ፤ ከሴቶች ኸዲጃ ቢንት ኹወይሊድ፤ ከተዳጊዎች ዐልይ ቢን አቢ ጧሊብ፤ ነፃ ከወጡ ባርያዎች መካከል ዘይድ ቢን ሐሪሣህ እና ባሪያ ከሆኑት መካከል ደግሞ ቢላል አል'ሐበሺይ ናቸው። አላህ ሁሉንም መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና።

መልስ - ዳዕዋ ሲያደርጉ የነበሩት ለሦስት ዓመታት ያህል በምስጢር የነበረ ሲሆን ከዚያም ዳዕዋውን በይፋ እንዲያደርጉ አላህ አዘዛቸው።

መልስ- ሙሽሪኮች ምእመናንን ወደ አቢሲኒያ ነጉሥ እንዲሰደዱ እስኪፈቀድ ደረጃ ድረስ በእርሳቸውና በሙስሊሞች ላይ ግፋቸውን አጧጧፉት።
ሙሽሪኮች ነብዩን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ለመጉዳት እና ለመግደል በአንድ ድምፅ ተስማምተውም ነበር። ይሁን እንጅ አላህ እሳቸውን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ከሙሽሪኮቹ ለመታደግ አጎታቸው አቡጧሊብን ከለላ አደረገላቸው።

መልስ- አጎታቸው አቡጣሊብ እና ባለቤታቸው ኸዲጃ ረዲየሏሁ ዓንሀ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።

መልስ - እድሜያቸው ሃምሳ ሲሆን ነበር። ያኔም ነው አምስቱ ሶላቶች በግዴታነት የተደነገጉላቸው።
ኢስራእ ማለት ከመስጅደል ሐረም ወደ መስጅደል አቅሷ ያደረጉት ጉዞ ነው።
ሚዕራጅ ማለት ደግሞ ከአል'አቅሷ መስጅድ ወደ ሰማይ እስከ ሲድራቲል ሙንታህ ድረስ ያደረጉት ጉዞ ነው።

መልስ - ከመዲና የሆኑ አንሷሮች እሳቸው ዘንድ መጥተው በሳቸው አምነው በዳዕዋውም እንደሚተባበሯቸው ቃል እስኪገቡላቸው ድረስ ሰዎች የሚሰባሰቡባቸው በዓላትና አጋጣሚዎችን ጠብቀው ሰዎች ፊት እየቀረቡ ዳዕዋ ያደርጉ ነበር፤ የጧኢፍ ሰዎችንም ዳዕዋ ያደርጉላቸው ነበር።

መልስ - ለአሥር ዓመታት ቆይተዋል።

መልስ - ዘካ፣ ፆም፣ ሐጅ፣ ጂሃድ፣ አዛን እና ሌሎችም የእስልምና ህግጋቶች በመዲና ሳሉ የተደነገጉ ናቸው።

መልስ - የታላቁ በድር ዘመቻ፤
የኡሑድ ዘመቻ፤
የአሕዛብ ዘመቻ፤
(ፈትሑ መካ) መካ የተከፈተችበት ዘመቻ፤

መልስ- ተከታዩ የላቀው አላህ ቃል ነው፦ {በእርሱም ውስጥ ወደ አላህ የምትመለሱበትንና ከዚያም እነርሱ የማይበደሉ ሲሆኑ ነፍስ ሁሉ የሠራችውን ሥራ የምትሞላበትን ቀን ተጠንቀቁ። 281} [ሱረቱል በቀራህ፡ 281]

መልስ - በአስራ አንደኛው አመተ ሂጅራ በወርሀ ረቢዑል አወል በስልሳ ሶስት አመታቸው አረፉ።

መልስ-1- ኸዲጃ ቢንት ኹወይሊድ ረዲየላሁ ዐንሃ፤
2- ሰውዳህ ቢንት ዘምዓህ ረዲየላሁ ዐንሃ፤
3- ዓኢሻህ ቢንት አቢ በክር አስ'ሲዲቅ ረዲየላሁ ዐንሃ፤
4- ሐፍሷ ቢንት ዑመር ረዲየላሁ ዐንሃ፤
5- ዘይነብ ቢንት ኹዘይማህ ረዲየላሁ ዐንሃ፤
6- ኡሙ ሰለማህ ሂንድ ቢንት አቢ ኡመያህ ረዲየላሁ ዐንሃ፤
7- ኡሙ ሐቢባ ረምላህ ቢንት አቢ ሱፍያን ረዲየላሁ ዐንሃ፤
8- ጁወይሪያህ ቢንት አል'ሓሪሥ ረዲየላሁ ዐንሃ፤
9- መይሙናህ ቢንት አል-ሓሪሥ ረዲየላሁ ዐንሃ፤
10- ሶፊያ ቢንት ሑየይ ረዲየላሁ ዐንሃ፤
11- ዘይነብ ቢንት ጀሕሽ ረዲየላሁ ዐንሃ፤

መልስ - ሦስቱ ወንዶች ልጆቻቸው፦
አል-ቃሲም፤ የነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ቅጽል ስማቸውም በእርሱው ነበር የተሰየመው (አበል ቃሲም ይባሉ ነበር)
ዐብደላህ፤
ኢብራሂም፤
ሴት ልጆቻቸው፦
ፋጢማህ፤
ሩቂያህ፤
ኡሙ ኩልሡም፤
ዘይነብ፤
ከኢብራሂም በቀር ሁሉም ልጆቻቸውን ከኸዲጃ (ረዲየላሁ ዐንሀ) የተወለዱ ናቸው። ከፋጢማህ በቀር ሁሉም እርሳቸው በህይወት እያሉ የሞቱ ሲሆን ፋጢማህ የሞተችው ግን እርሳቸው ከሞቱ ከስድስት ወር በኋላ ነበር።

መልስ - ረዥምም አጭርም ያልሆኑ በሰዎች መካከል መካከለኛ ቁመት፤ የአላህ ሶለዋትና ሰላም ይስፈንባቸውና ነጭ ሆኖ ቅላት የጠጣ ፊት ነበራቸው። ወፍራም ፂም፣ ሰፋፊ ዓይኖች፣ ተለቅ ያለ አፍ፣ ፀጉራቸው እጅግ የጠቆረ፣ ትከሻቸው የሰፋ እና ደስ የሚል መአዛ እንዲሁም ከዚህም ውጭ የመልካም ተክለ ሰውነት መገለጫ ባህርይ ነበራቸው።

መልስ - ነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ኡመታቸውን ጥፋ ያለው ካልሆነ በቀር በማይሳሳትበት ነጭ ሆኖ ፍንትው ባለ ግልፅ ማስረጃ ላይ ነው የተውት። የትኛውንም ኸይር ነገር ኡመታቸውን ጠቁመዋል፤ ከየተኛውም ሸር ነገር ደግሞ ኡመታቸውን አስጠንቅቀዋል።